የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መልቀቂያ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ገዱ አንዳርጋቸው


የአማራ ክልል ምክር ቤት እያደረገ ባለው ስብሰባ ጥያቄያቸውን ተቀብሏል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለፓርቲያቸው የመልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ነው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ጥያቄያቸውን የተቀበለው፡፡

የመልቀቂያቸውን ምክንያትም አዴፓ ለአማራ ክልል ምክር ቤት እያቀረበ ነው፡፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልልን ከታኅሳስ 2006. ጀምሮ በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል፡፡

ምክር ቤቱ መልቀቂያውን ተቀብሎ አዲስ ርዕሰ መስተዳድር በእጩነት አቅርቧል፡፡
ፓርቲው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት ያቀረባቸው ዶክተር አምባቸው መኮንን ነው፡፡
ዶክተር አምባቸው መኮንን

በተመሳሳይ ዶክተር አምባቸው መኮንን ሲሳይ ደግሞ በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆኑ በዕጩነት ቀርበዋል፡፡


Post a Comment

0 Comments