![]() |
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አለማየሁ እጅጉ/ ፎቶ በአረጋዊ ሰሎሞን |
ር ድረስ የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
መስከረም አምስት ከሌሊቱ 9ሰዓት ላይ በአካባቢዎቹ በተደረገው ጥቃት ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ የ23 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በርካቶች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ሸሽተዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ እንዳሉት በጥቃቱ ወቅት የፌደራል ፖሊሶች በስፍራው ቢደርሱም "ወደ ውስጥ ለማለፍ አልተፈቀደልንም" በማለት ሊታደጓቸው አልቻሉም፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አለማየሁ እጅጉ ከኢቲቪ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የክልሉ ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን እና ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ በስፍራው ቢደርስም ቦታው አመቺ እንዳልነበር ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራሉ ዛሬ መስከረም ስድስት ምሽት ላይ ለዋልታ ቴሌቪዥን እንደገለፁት በግጭቱ 23 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በግድያው ላይ የተሳተፉ 70 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጥቃቱች መፈፀማቸው የሚታወስ ሲሆን ዜጎች እምነት የጣሉበት የህግ የበላይነት ሊታደጋቸው ባለመቻሉ እና በመንግስት በኩልም ምላሾች ባለመሰጠታቸው ቅሬታቸውን እየገለፁ ነው፡፡
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን