በትናንትናው ዕለት (ረቡዕ )በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የፍትህ መፅሄት ዋና አዘጋጅና ባለቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው እለት መፈታቱን ቢቢሲ ከወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ መረዳት ችሏል።
በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 5፣ 2013 ዓ.ም ጥዋት በእስር ላይ የነበረበት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመጠየቅም ሲያመራ መግባት አይቻልም ተብሎ እንደነበረና ፍርድ ቤት ሊያቀርቡት ይችላሉ በሚል እሳቤም እዛው እየጠበቁ የነበረ ቢሆንም ተፈትቶ ማየቱን አስረድቷል።
ከሱ በተጨማሪ የፍትህ መፅሄት አዘጋጁ ምስጋናው ዝናቤም መፈታቱን ታሪኩ አክሎ ገልጿል።
ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋለም ይሁን የተፈታተበትም ምክንያትን በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ እስካሁን እንዳላገኙም ታሪኩ ያስረዳል።
በትናንትናው ዕለትም ታሪኩ ለጥቂት ደቂቃዎች እንዳገኘውና ለምን እንደታሰረ በጠየቀው ወቅት "የሐሰት ወሬ በማሰራጨት ትፈለጋለህ ከሚል ውጪ የነገሩኝ ነገር የለም።" ማለቱንም ታሪኩ አስረድቷል።
ምንጭ :- ቢቢሲ
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን