ከ40 በላይ የሚሆኑ በቀድሞ ስሙ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የሚባለዉ ተቋም ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ፡፡
የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ለስብሰባ ከተጠሩበት ስፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
እንደ ጋዜጣዉ ገለጻ፣ ከፍተኛ አመራሩና የደኅንነት አባላቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ገርጂ አካባቢ በሚገኘውና ቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ተብሎ ይጠራ በነበረውና አሁን የኮርፖሬሽኑ ንብረት በሆነው አሞራው ሕንፃ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉበት ምክንያት ባይገለጽም፣ የፌዴራል ፖሊስ ጊዜያዊ እስር ቤት በሆነው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማቆያ ቤት መታሰራቸውን ምንጮቹ አክለዋል፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን