አፍሪካ ህብረት ከመጪው የፈረንጆች አመት መጀመሪያ ጀምሮ በሶማሊያ አልሸባብ የሚገኝባቸው ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ነጻ እናደሚያደርግ ገለ



በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በሶማሊያ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ንብረት እያወደመ ያለው አሸባሪው ቡድን አልሸባብ አሁንም በሃገሪቱ ላይ እየፈፀመ ባለው የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡

ቡድኑ የሚያደርሳቸውን ጥቃቶች ተከትሎ አፃፋዊ ምላሾች ቢፈፀምበትም አሁንም ግን ጥቃት ከመፈፀም አልታቀበም፡፡

የአልቃይዳ ክንፍ የሆነው ይህው አሸባሪ ቡድን ትናንት በሞቃድሾ የፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት አቅራቢያ ባደረሰው ሁለት የቦንብ ጥቃት የ20 ሰዎች ህይወት አልፎ 40 ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታው ምክር ቤት አዲስ እቅድ አፅድቋል፡፡
እቅዱ በሶማሊያ የተለያዩ አካባቢዎች አሁንም ድረስ በአልሸባብ የተያዙ ስፍራዎችን ከቡድኑ ነፃ ማውጣት መሆኑን ዘኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡

በፈረንጆቹ 2019 መጀመሪያ አካባቢ ወደ ተግባር ይገባል በተባለው በዚሁ ጥምር ዘመቻ ላይ የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር እና የጁባላንድ ግዛት ሃይል ይገኙበታል፡፡

በህዳር ወር የፀደቀው ይህው አዲሱ እቅድ ለአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በሶማሊያ(አሚሶም) ዘመቻዎች መመሪያ በመሆን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ያገለግላል፡፡
መካከለኛው ጁባ የተባለው አካባቢ በጌዶ፣ በባይ፣ በታችኛው ሸበሌ እና በህንድ ውቂያኖስ የሚዋሰን ሲሆን አልሸባብ የመሸገበት ስፍራ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የአሚሶም ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሪቻርድ ኦምዌጋ እንዳሉት ዘመቻው የሶማሊያ የሽግግር ጊዜ አንዱ እቅድ ሲሆን በቀጣይ ሶማሊያ አቅሟን አጠናክራ ራሷን ከፀጥታ ስጋት እንድትጠብቅ የሚደርግ ነው፡፡




Post a Comment

0 Comments