የመፃተኛው ኑዛዜ በውቀቱ ስዩም poet Bewketu Seyoum. #AS_production


የመፃተኛው ኑዛዜ
 በውቀቱ ስዩም
ካገር ጫፍ እስከ ጫፍ በጥላህ ከልለህ
"ተራራው የኔ ነው" ለምን ትለኛለህ?
"ወንዙ ድርሻዬ ነው" ለምን ትለኛለህ?
እንኳንስ መሬቱ አንተም 'ንተ አይደለህ!!!
።።።።
እኔ መፃተኛ ፣አንተ "ኗሪ ነኝ" ባይ
እኔ እግሬን ስከተል ርስትህን ስታይ
ስቀርብህ ገፋኸኝ ስትገፋኝ ቦታ አጣሁ
ድንኳን ብትተክል፤ ነፋስ ሆኜ መጣሁ፡፡
።።።።
'ባትህ 'ባቴ
ጠበኛ ስማቸው
ጠበኛ ህልማቸው
በህይወት ተጣሉ ታረቁ ባፅማቸው
'ፈር ተቃቃሩ አፈሩ አስማማቸው
በዙሪያቸው በቅሎ ከቧቸው ሞት ደኑ
መተቃቀፍ መርጠው ማማና ወይን ሆኑ፡፡
።።።።
"
ይችላል" ይሉሀል ፍልሚያ ማዘጋጀት
'ባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት።
።።።።
አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወደቅክ
አካሌ ደረቴ መሆንህን መች አወቅክ?!
።።።።።

Post a Comment

0 Comments