ሰሜን ኮሪያ የተጣሉባትን ማእቀቦች እየጣሰች መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ገለፀ፡፡



በተባበሩት መንግስታት የባለሙያዎች ቡድን ባወጣው ሪፖርት ሃገሪቱ ነዳጅ በገፍ ከማስገባት እስከ ባንኮችን ድረስ ማእቀቡን ጥሳለች ብሏል፡፡


ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ሙከራ ካደረገችበት ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክርቤት በርካታ መማእቀቦች ተጥለውባታል፡፡ ሀገሪቱ የኒውክሌር ሙከራዎቿን በደጋገመች ቁጥር የማእቀብ አይነቶች በርከት በለው በመጣላቸው ምጣኔ ሃብቷን አቀዛቅዞ ከቀሪው የዓለም ሃገራት ጋር የነበራትን ግንኙነት በእጅጉ እንዲጠብ አድርጎታል፡፡

የኋላኋላ ሃገሪቱ በሯን ለድርድር ክፍት አድርጋ በተለይም ከቀንደኛ ባላንጣዋ አሜሪካ ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙነት ለማስተካከል እየታተረች ነው፡፡ 

የኒውክሌር ማብለያ ጣብያዋን እንዳወደመች ስትናገር የቆየችው ፒዮንግ ያንግ በፈረንጆች የዘመን ቀመር በ1950ዎቹ በአሜሪካ የተጣለባት ማእቀብ እንዲነሳ ስትጠይቅ ቆይታለች፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ፒዮንግያንግ የኒኩሌር ማብለያ ጣቢያዋን አሁንም ሙሉ በሙሉ ልትዘጋ ይገባል በማለት ማእቀቡን አላነሳችም፡፡
የተባበሩት መንግስታት የባለሙያዎች ቡድን ባወጣው ባለ 400 ገፅ ሪፖርት ሃገሪቱ መርከቦችን በመጠቀም ነዳጅ በገፍ ከማስገባት ጀምሮ እስከ የተለያዩ ሃገሮች በንኮችን መበርበር እና የጦር መሳሪያዎችን ደግሞ ለየመን እና ለሱዳን ጭምር በመሸጥ ማእቀቡን ጥሳለች ብሏል፡፡

እጅግ ውስብስብ በሆነ መልኩ ማእቀቦቹን በመጣስ ድርጊተቹን መፈጸሟን የሚያሳየው የመንግስታቱ ሪፖርት የከሰል ድንካይ እየቸበቸበች መሆኑንም ይፋ አድርጓል፡፡

ፒዮንግ ያንግ ለኒውክሌር መሳሪያዋ እነ ለተወንጫፊ ሚሳኤል ስራዎቿ ገንዘብ እንዳታገኝ ለማድረግ ማእቀቡ እንደተጣለባት የገለፀው የተባበሩት መንግስታት ሃገሪቱ ግን ስልቷን በመቀየስ በተወሳሰበ መልኩ ማእቀቦቹን ጥሳለች ብሏል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የባለሙያዎች ቡድን ሀላፊ በ15 ዓመታት ስራው የዚህ ዓይነቱ ውስብስብ ተግባር ገጥሞት እንደማየውቅ ለኤን ቢሲ ተናግሯል፡፡




Post a Comment

0 Comments