አልጀዚራ የሃገሪቱን ዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘገበው ሳዑዲ አረቢያ እእረኞቹን ለጊዜው
ብትለቅም ጉዳያቸውን ግን አሁንም እየመረመረች ነው፡፡
ከዓመታት በፊት ሳዑዲ አረቢያ ለሴቶች
መብት መከበር ከማይመቹ የዓለም ሃገራት ተርታ ስሟ ተደጋግሞ ሲነሳ ቆይቷል፡፡ ተሸከርካሪዎችን ከማሽከርከር ጀምሮ ሌሎች የተለያዩ
መብቶች ለወንዶች ብቻ በመፍቀድ ለሴቶች የተከለከሉ በርካታ ተግባራት እንዲስተካከሉ ከፈቀደች አንድ ዓመት እንኳን አልሞላትም፡፡
ምንም እንኳን ሃገሪቱ ቀድመው በሴቶች
ላይ ተጥለው የነበሩ ስታዲየም እንዳይገቡ፣ ሲኒማ እንዳይመለከቱ እና እንዳያሽከረክሩ የሚከለክለውን ህግ ብታነሳም አሁንም ግን በርከት
ያሉ መብቶችን ለሴቶች ከልክላለች፡፡
የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ መኪና መግዛት
እና ፍች የመፈፀም መብት አሁንም ለሴቶች አልተሰጡም፡፡ በመሆኑም ሃገሪቱ የወንዶች ዓለም ተብላ እንድትጠራ አድርጓታል፡፡
ይህ የመብት ክልከላ ግን በበርካቶች
ዘንድ ሰላማዊ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ሃገሪቱን ለቀው የወጡ ሴቶችም መመለስ እንደማይችሉ ቢመለሱም ግን ዘብጥያ እንደሚወርዱም ደጋግመው
ይናገራሉ፡፡ እዚያው ሳኡዲ አረቢያ ሆነው ለሴቶች መብት ጥብቅና የቆሙ ዜጎች በሙሉ ዘብጥያ መውረዳቸው ደግሞ አንዱ ማሳያ ተደርጎ
ይነሳል፡፡
አልጀዚራ የሳዑዲ አረቢያ ዜና አገልግሎትን
ጠቅሶ እንደዘገበው ለአለም አቀፍ ሪፖርተሮች እና ዲፕሎማቶች ዝግ በነበረው የሃገሪቱ ችሎት ላይ እስረኞቹን ለጊዜው ብትለቅም ጉዳያቸውን ግን አሁንም እየመረመረች ነው፡፡
ትናንት ለጊዜው ከእስር የተለቀቁት ሶስት የመብት ተሟጋቾች ስማቸው ይፋ ባይሆንም ጦማሪ ኢማን አል ናፍጃን፣ አዚዛ አል የሱፍ እና በኪንግ ሳኡዲ
ዩኒቨርሲቲ መምህርት የነበሩት ሮቃይ አል ሞሃረብ ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ፡፡
ቀረቤታ ያላቸው ግለሰብ ለአጃንስ ፍራንስ ፕረስ እንደገለፁት ከእስር የተፈቱት እንስት የመብት ተሟጋቾች
በቀጣይ ወር ለፍርድ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን