የቀድሞው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት / ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::

/ ነጋሶ 1987 እስከ 1994 ዓም ጀምሮ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡


/ ነጋሶ በወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ ባለመስማማታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ከለቀቁ በኋላም በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ በግል ዕጩነት የሕዝብ ድምጽ በማግኘት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆንም አገልግለዋል፡፡

ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ደሲቱ ቀጀላ ሁለት ልጆችን ወልደዋል፡፡
በትምህርት እድል ከጀርመን ጎተህ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪአቸውን ያገኙት ዶ/ር ነጋሶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የታሪክ መምህር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

በጀርመን ሃገርም ረጊና አበልት የተባሉ ጀርመናዊት ነርስ እና አዋላጅ ጋር ትዳር በመመስረት አንድ ልጅ ወልደዋል፡፡

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር አባል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ በሽግግር ወቅት የማስታወቂያ ሚኒስትር በመሆን እንዲሆን የያኔው ኦፒዲኦ ያሁኑ ኦዲፒ ማእከላዊ  ኮሚቴ አባል በመሆንም ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡


የመድረክ መስራች እና በኋላም የአንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ሆነውም ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ከዛም ከፖለቲካው ዓለም ራሳቸውን በማግለል የተለያዩ ጥናታዊ ፅሑፎችን በመስራት ሲያቀርቡም ቆይተዋል፡፡

የሶስት ልጆች አባት የሆኑት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በስኳር ህመም እና በደም ግፊት ምክንያት በሳኡዲ አረቢያ በአሜሪካ እና በመጨረሻም በጀርመን ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በ በ76 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል፡፡

(AS ዘ ብሔረ ጦቢያ)

Post a Comment

0 Comments