ሰበር በአማራ ክልል የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገ



በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ‹‹የመፈንቅለ መንግስት››
 ሙከራ መደረጉን የጠቅላይ ሚንስትር ፕሬስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ፡፡

በክልልሉ ዛሬ በተደራጀ ሁኔታ በመንግስት መዋቅር ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መሞከሩን አቶ ንጉሱ ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ‹‹መፈንቅለ መንግስት›› በማካሄድ የመሪ ድርጅቱ አዴፓ እና የአማራ ክልል ህዝብ ያገኘውን ነፃነትና ሰላም ለመንጠቅ እንዲሁም በህዝቡና በመንግስት ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተደራጀ እንቅስቃሴ መደረጉንም ነው አቶ ንጉሱ የገለፁት፡፡

የተደረገውን ‹‹የመፈንቅለ መንግስት›› ሙከራ የፌደራል መንግስት የፀጥታ መዋቅር ክልሉን በተለይም ባህርዳር ከተማና አካባቢውን በቁጥጥር ስር አውሎ በተግባሩ የተሳተፉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ትእዛዝ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡

ህብረተሰቡም አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ebc

Post a Comment

0 Comments