ምርጫ ቦርድ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ሕዝበ ውስኔ የሚሰጥበትን ቀን ይፋ አደረገ
ምርጫ ቦርድ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔ መስጫ ቀን ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ. ም እንዲሆን መወሰኑን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ። ቦርዱ ከነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ 8,460 ምርጫ አስፈጻሚዎችን እንዲሁም 1,692 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎችን እንደሚያደራጅም አስታውቋል። ቦርዱ ለሕዝበ ውሳኔው ሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልገውን 75 ሚሊዮን 615 ሺህ ብር የደቡብ ክልል ምክር ቤት እንደሚሸፍንም ተገልጿል።
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን