የሶሪያ መንግስት ይህን ውሳኔ የወሰነው ቱርክ እየወሰደች ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻን ለመከላከል ነው፡፡
ቱርክ ‹‹ደህንነቱ የተጠበቀ›› ስፍራ ለመፍጠር በሚል በርካታ ሶርያውያን ስደተኞች በሚገኙበት ሰሜን ሶሪያ ላይ ከባድ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች አንድ ሳምንት አስቆጥራለች፡፡
ሰሜን ሶሪያ የነበሩ 1ሺህ የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች ስፍራውን ለቀው በወጡ ማግስት ቱርክ አሸባሪ ባለችው የኩርድ ወታደር ላይ በምድር ጦር እና በአየር ሃይል ማጥቃቷን ቀጥላለች፡፡
በወታደራዊ ዘመቻውም እስካሁን በኩርዶች በኩል ከ50 በላይ ንፁሃን እና 100 ወታደሮች ሲገደሉ በቱርክ በኩል ደግሞ 4 ወታደሮች እና ስምንት ንፁሃን እንዲሁም 16 የቱርክ ደጋፊ ሶሪያውያን ህይወታቸውን ገብረዋል፡፡
በተባበሩት የሰብአዊ ተራድኦ 160ሺህ ዜጎች እንደተፈናቀሉ ቁጥሩም እየጨመረ እንደሚሄድ ገልጿል፡፡
በሳምንት ውስጥ ይህን ያክል ጉዳት ያስከተለውን ወታደራዊው ዘመቻ ለማስቆም ደግሞ ኩርድ ወታደሮች ለብቻ የሚቻላቸው አይመስልም፡፡ በመሆኑም ሶሪያ ኩርዶችን ለመደገፍ ወታደሮቿን ወደ ቱርክ ድንበር ለመላክ ተስማምታለች፡፡
በኩርድ የሚመራው አስተዳደር ከሶሪያው ፕሬዝዳንት በሺር አል አሳድ ጋር እንደተደራደሩ እና የቱርክን ወታደራዊ ጥቃት ለመመከት ወታደራዊ ድጋፍe እንደሚደረግለት በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ማስፈሩን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
የኩርድ አስተዳደር ‹‹በቱርክ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ለመመከትና ለመጋፈጥ የሶሪያ ወታደሮች ወደ ሶሪያና ቱርክ ድንበር በመላክ ሊያግዙን ተስማምተናል፡፡›› ማለቱን አልጀዚራ አስነብቧል፡፡
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን