"የአንበጣ መንጋ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው" |#Aregawi_Solomon_AS




በ2011/ 2012 የምርት ዘመን ከተዘራው ሰብል ውስጥ 40 በመቶው መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡
ከቅርብ ወራት ወዲህ ከየመን እና ከሶማሊያ የመጣው የአንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ በ61ወረዳዎች ላይ ተከስቶ በሰብል ላይ መጠኑ ያልታወቀ ቀላል ጉዳት አድርሶ እንደነበርና ህብረተሰቡ ባደረገው ሰፊ እንቅስቃሴ አማካኝነት መንጋው የከፋ ጉዳት አለማድረሱንም የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ በቀጣይም ጥሩ የምርት ይዘት ባለው ሰብል ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል የዝናብ መጠን እና አዲስ የአንበጣ መንጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ የደረሱ ሰብሎችን በመተጋገዝ ሊሰበስብ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ምርት ሲሰበሰብ ዝናብንና አንበጣን በመስጋት ያልደረሱ ሰብሎችን እንዳይሰበስብ ሊጠነቀቅ እንደሚገባም አስጠንቅቋል፡፡

Post a Comment

0 Comments