በ1962 ዓ.ም የተመሰረተው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከአ.አ. በ4ዐዐ ኪ.ሜ ርቀት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይገኛል፡፡ ስፋቱ ወደ 22ዐዐ k.m2 የሚደርስ ሲሆን ከሰሜን ወደ ደቡብ 74 ኪ.ሜ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ደግሞ 53 ኪ.ሜትር ይሰፋል፡፡ ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ ከ145ዐ እስከ 4377 ጫማ ባለ ልዩነት ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎችን ያካትታል፡፡ 4377 ጫማ የሚረዝመው እና ከኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የቱሊ ዲምቱ ተራራን ጨምሮ የአፍሮ አልፓይን ከፍተኛ ቦታዎች በዚህ ፓርክ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የባሌ ተራሮች ከፍተኛ አካባቢ በተለያዩ መንገድ የተፈጠሩ ሀይቆች፤ እርጥበት አዘል መሬቶች፣ የእሳተጎሞራ ቅሪቶችን አቅፎ ይዟል፡፡
ፓርኩን ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነገር በኢትዮጵያ ትልቁና ወደ ሰባት ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሚሸፍነው ‹‹የሐረና ደን›› በውስጡ በመገኘቱ ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንድ ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሆነው በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ሲገኝ የተቀረው ስድስት ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር ድርሻ በኦሮሚያ ክልል የደንና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ ይተዳደራል፡፡ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ጊዜያዊ መዝገብ ውስጥ ተካቷል፡፡
ከዚህም ሌላ ከ1600 በላይ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ዓይነት ዕፅዋቶች፣ 78 ዓይነት አጥቢ የዱር እንስሳትና ወደ 200 የሚጠጉ አእዋፋት በፓርኩ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል 32 ዓይነት ዕፅዋቶች፣ 31 የሚጠጉ ብርቅዬና ድንቅዬ የዱር እንስሳትና ወደ ስድስት የሚጠጉ ዕፅዋት በብሔራዊ ፓርኩ ካልሆነ በስተቀር በሌላው ዓለም ፈጽሞ አይገኙም፡፡ በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ ከሚገኙ 78 የሚደርሱ አትቢ የዱር እንሰሳት 17 የሚሆኑት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ እንሰሳት ናቸው፡፡
ከዚህ ባሻገር ለሳይንስና ኢኮሎጂ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው በደረታቸው የሚሳቡ ልዩ ልዩ እንስሳትና መንቆረርቶችን ፓርኩ አቅፎ ይዟል፡፡ ቡናና በኢትዮጵያ ውስጥ ለባህል መድኃኒትነት የሚውሉ 40 ከመቶ ዕፅዋቶችም ይገኙበታል፡፡ በእፅዋት እና በእንሰሳት ብዝሃ ህይወት መበልፀግ ደረጃ ፓርኩ ከአለም 34ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የባሌ ብሄራዊ ፓርክ በ “Bird lite International” በአለም ከሚገኙ አስፈላጊ የአዕዋፍ መኖሪያ ቦታዎች ጎራ ተመድቧል፡፡
በፓርኩ ከ28ዐ በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች ሲኖሩ ሲሆን ሰባቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፡፡እንደ ዓለም አቀፍ የወፎች ድርጅት ሪፖርት ከሆነ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የአፍሪካ አራተኛው ‹‹በርዲንግ ሳይት›› ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ በባሌ ብሄራዊ ፓርክ ዋቢ ሸበሌ፣ ዌብ፣ ዱማል፣ ያዶት እና ወልመል የተሰኙ ወንዞች ይፈሳሉ፡፡ በባሌ ብሄራዊ ፓርክ ከሚገኙ የዱር እንስሳት መካከል ቀይ ቀበሮ፣ኒያላ ፣ አጋዘን እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡
Located 400km southeast of Addis Ababa, Bale Mountains National Park contains a spectacularly diverse landscape. The high altitude, afro-montane Sanetti Plateau rises to over 4,000m and includes the highest peak in the southern Ethiopia highlands. This undulating plateau is marked by numerous glacial lakes and swamps and surrounded by higher volcanic ridges and peaks. The southern slopes are covered by the lush and largely unexplored Harenna Forest.
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን