ኢትዮጵያን ላለፉት #10_ዓመታት የመሯት ሰዎች በሶማሌ ክልል የሚኖሩ ሴቶች እንዲደፈሩ፣ የክልሉ ነዋሪዎች እንዲገደሉ፤ እዲዘረፉ፣ እንዲሰደዱ፣ በእስር እንዲማቅቁ፣ ስራቸውን እንዲያጡ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲቃጠሉ፣ ካህናት እና ምእመናን እንዲሰዉ፣ የክልሉ ተወላጆች ስማቸው እንዲጠፋ፣ በታሪክ መጥፎ ጠባሳ እንዲኖራቸው አድርገዋል፡፡
አብዲ ኢሌ ይህን እንዲያደርግ የልብ ልብም ሰጥተዉታል፡፡
የስንቱን ምስኪን ጀርባ ሲያጠኑ እና ሲያስጠኑ የነበሩት፣ ተቃዋሚያቸውን ጥላሸት ሲቀቡ የኖሩት መሪዎች ይህ ሰው በግልፅ ግፍ እንዲሰራ ረድተዉታል አልያም ግፍ ሲሰራ አይተው እንዳላዩ ሆነዋል ፡፡
አብዲ ኢሌ ብቻዉን ይህን አላደረገም! እንደውም ዋነኞቹ መሪዎቹ ነበሩ እንጂ!
ታሪክ ራሱን ካልደገመ የአሁኑ እንዳያልፍ አልፏል፤ የመሪዎቹ ድርጊት ግን በማይጠፋ ቀለም ተከትቦ ለታሪክ ህያው ይሆናል፡፡
አሁንም የሰውየው ከስልጣን መነሳት የሚያንገበግባቸው ሙጣጮች አሉ፡፡ እነሱም አንድ ቀን ወደ ቀልባቸው ሲመለሱ የላሸቀ ሐሳብ እንደነበራቸው ይገባቸው ይሆን ይሆናል፡፡
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን