
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ ማጠናቀቁን ተከትሎ ነው አቶ አህመድ ሽዴን ሊቀ መንበር አድርጎ የመረጠው።
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ስብሰባው በክልሉ ተፈጥሮ በነበሩው ሁኔታ ላይ መገምገሙም ተነግሯል።
በክልሉ ከሐምሌ 20/2010 ጀምሮ በተከሰተው ግጭት የበርካቶች ህይወት ያለፈ ሲሆን ሰባት አብያተ ክርስቲያናት እና የንግድ ቋማት ተቃጥለዋል፡፡
በተለይ በጂግጂጋ ከተማ ላይ የሚገኙ በርካታ የግለሰብ ንብረቶች ተዘርፈዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ከሶስት ቀን በላይ ለረሃብ መጋለጣቸው ይታወሳል፡፡
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን