በሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 7 አንበሶች በረሃብና በሕክምና እጥረት ሞተዋል



courtesy: hiwotebeAddis

“በሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 7 አንበሶች በረሃብና በሕክምና እጥረት ሞተዋል፡፡ ያሉትም ቢሆኑ ከስተው አጥንታቸው ከቆዳቸው ጋር ተጧብቋል፡፡ ተነስተው ለመንቀሳቀስም ሲቸግራቸው አይተናል…”


የአንበሳ ጊቢ ታድሶ በዘመናዊ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ በሚል የእድሳት ስራው የተጀመረው ከሁለት ዓመት በፊት መሆኑ ይታወቃል፡፡

በ9 ወራት ይጠናቀቃል የተባለው እድሳት አሁን ገና 14 በመቶ ላይ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ በእድሳቱ መዘግየትና በግቢው ውስጥ የሚኖሩ አንበሶችና ሌሎች እንስሳት አያያዝም አሳሳቢ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡

በሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 7 አንበሶች በረሃብና በሕክምና እጥረት ሞተዋል፡፡

ያሉትም ቢሆኑ ከስተው አጥንታቸው ከቆዳቸው ጋር ተጧብቋል፡፡ ተነስተው ለመንቀሳቀስም ሲቸግራቸው አይተናል፡፡
በጊቢው ያሉ ሁለት ጭላዳዎችም የጀርባቸው ፀጉር ተመልጧል፡፡

እንዲህ ያለውን ቅሬታ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ለከንቲባ ፅህፈት ቤትና ለአዲስ አበባ ቱሪዝም ቢሮ ባቀረቡት መሰረትም የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች የአንበሳ ጊቢን ጎብኝተዋል፡፡

ይህን ተከትሎ የአንበሳ ግቢ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሴ ክፍሎም ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡
ስራ አስኪያጁ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ በደብዳቤ የገለፁላቸው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ተከለ ኡማ መሆናቸውን የዘገበው ሸገር ነው፡፡

Post a Comment

0 Comments