ቀድሞ በክልሉ የመንግስት ባለሥልጣናት የነበሩ፣ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች፣ በክልሉ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ሲሰሩ የነበሩ አስተማሪዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ ነጋዴዎች ወዘተ. በክልሉ የመብት ጥሰት በሰፊው እንዳለ፤ ክልሉን የሚያስዳድሩ ሰዎች በትምህርት ያልታገዙ(ማንበብም መፃፍም የማይችሉ)፣ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ አውግተውኛል፡፡
በተለይ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አብዱል ፈታሕ ማሕሙድ "በክልሉ ስላለው የመብት ጥሰት በካቢኔ በኩል እውነታነቱ ቢረጋገጥም በፌደራል ደረጃ ግን ምላሽ ሳይሰጠው አራት አመት አስቆጥሯል ብለውኛል፡፡"
በዚሁ ምክንያትም በርካቶች ከስራ ተወግደው ለእስራትም ተዳርገዋል፤ ችግር ፈጣሪዎች ግን አሁንም ስልጣን ላይ ናቸው ሲሉም በቁጭት ነግረውኛል፡፡
"እኛ በክልሉ ላይ የሚፈፀሙ የህግ ጥሰቶችን በተመለከተ ለፌደራል መንግስት ሪፖርት ስናደርግ የፌደራል መንግስት ሪፖርቱን ለአብዲ ኢሌይ ይሰጥ ነበር፡፡ የሰውየው(የአብዲ ኢሌ) አካሄድ ከክልል አልፎ ለሃገርም ጉዳቱ ከባድ እንደሆነም በተደጋጋሚ ስናሳውቅ መንግስት እንዳልሰማ ይሆን ነበር፡፡ የዚህ ሁሉ ተጠያቂም የፌደራል መንግስት ነው፡፡" ሲሉ ያጫወቱኝ ደግሞ ሌላኛው የቀድሞ ጉምቱ ባለ ስልጣን ናቸው፡፡
የክልሉ ባጀት የግለ ሰቦች ማደለቢያ ሲሆን እየታየም ዝም ተብሏል ሲሉም በቁጭት ነግረውኛል፡፡
"ነፍሰ ጡሮች በምጥ ሲሰቃዩ አምቡላንሶች ግን ጫት ማመላለሻ ሆነዋል።" ያለኝ ደግሞ የክልሉ ተወላጅ ወጣት ነው፡፡ የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ደግሞ የአብዲ ኢሌ (አብዲ ሞሐመድ ዑመር) ልሳን እንደሆነም እያዘነ ነግሮኛል፡፡
ሁሉም ግን የኢትዮጵያ መንግስት ከህዝቡ ይልቅ የክልሉን ፕሬዝዳንት ያስቀድም ነበር ብለውኛል፡፡
ከክልሉ ተወላጆች ጋር በነበረን አጭር ጊዜ ብዙ ነገሮችን አጫውተውኛል፡፡
አሁን ከብዙ አሳዛኝ ድርጊቶች በሇላ አብዲ ኢሌ ከስልጣን ተነስቷል፡፡
የክልሉ ስልጣን አጠቃቀም እና የመንግስት ለዘብተኝነት መጥፎ ጠባሳ አስቀርቶብናል፡፡ ይህ ለወደፊት ትምህርት ሊሆን ይገባል፡፡
ዝምታና መሸፋፈን ጉዳት እንጂ ፋይዳ የለውም፡፡
የክልሉ ስልጣን አጠቃቀም እና የመንግስት ለዘብተኝነት መጥፎ ጠባሳ አስቀርቶብናል፡፡ ይህ ለወደፊት ትምህርት ሊሆን ይገባል፡፡
ዝምታና መሸፋፈን ጉዳት እንጂ ፋይዳ የለውም፡፡
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን