‹ሜዲካል
ቻሪቲ ዊዝአውት ቦርደርስ› የተባለ ምግባረ ሰናይ የጤና ተቋም እንደገለፀው በደቡብ ሱዳን ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ 125 ሴቶች
መደፈራቸውን ገልጿል፡፡
ሩት ኦኬሎ
የተባሉ በደቡብ ሱዳን አዋላጅ በተለይ ባለፉት ሳምንታት በርካታ ሴቶችና ህፃናት በንቲዩ በተባለ አካባቢ ወደሚገኘው የተቋሙ ክሊኒክ
መሄዳቸውን ገልፀው በፆታዊ ጥቃቱ ‹የሚዘገንን› ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ተናግረዋል፡፡
አዋላጇ
አክለውም እድሜአቸው ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ልጃገረዶችን ጨምሮ ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች እና ነፍሰ ጡሮችም ሳይቀር
የአስገድዶ ደፋሪዎቹ ሰለባ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡
በሃገሪቱ
ዜጎች እና በውጭ ሃገር የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እየተፈፀመ ባለው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ላይ የወታደሮች ሚናም እንዳለበት
ዘገባው ጠቅሷል፡፡
ባለፈው
መስከረም ወር ላይ የደቡብ ሱዳን ፍርድ ቤት በውጭ ሃገር ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅመዋል ባላቸው 10 ወታደሮች
ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በደቡብ
ሱዳን ከሚገኙ እንስቶች ውስጥ 65 በመቶዎቹ ፃታዊና የጉልበት ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡
በእርስ
በእርስ ግጭት ምክንያት ላለፉት 5 ዓመታት የጦር ምድር ከሆኑ የደቡብ ሱዳን አካባቢዎች አንዱ በሆነው በንቲዩ ውስጥ የሚኖሩ የምግብ
ድጋፍ በሚሹ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ እየደረሰ ያለው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን የዘገበው አጃንስ
ፍራንስ ፕረስ ሴቶቹ ከመደፈር በተጨማሪ ግርፋት እና ሌሎች የጉልበት ጥቃቶች እየደረሰባቸው መሆኑንም አስነባቧል፡፡
የደቡብ
ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ከጀመረበት ከ2013 ጀምሮ እስካሁን ከ180ሺ በላይ ዜጎች ተገድለው ሚልየኖች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን