ዋልታ ይቅርታ የጠየቀው የትግራይ ክልል መንግስት ህዳር 16/2011 ዓ.ም በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱትን ሰልፎች ተከትሎ በኮርፖሬቱ የተሰራው ዘገባ ‹የህዝብ ድምፅ ለማፈን› ሆን ተብሎ ‹ተቀይሮ› የተሰራ ነው በማለቱ ነው፡፡
በመሆኑም ተቋሙ ዘገባውን አርሞ እንዲቀርብ እና ይቅርታ እንዲጠይቅ በላከው ደብዳቤ ምክንያት ነው ዋልታ ይቅርታ የጠየቀው፡፡
‹‹የሰልፉን አላማ በማዛባት የትግራይ ህዝብ ድምፅ በማፈን የህዝቡ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥቄ አንግበው ሰልፍ እንደወጡ አስመስላችኋል›› ሲል ክልሉ ለተቋሙ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡
‹‹ዘገባው የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄ የሚል ትርጓሜ ያለው ዘገባ በመስራታችን ይቅርታ እንጠይቃለን›› ብሏል ዋልታ ቴሌቪዥን፡፡
የቴሌቪዥን ጣቢያውም ከድምፂ ወያኔ ቴሌቪዥን የተላከለትን ዘገባ በዜና ሰዓቱ ላይ አቅርቧል፡፡
![]() |
የትግራይ ክልል መንግስት ዋልታ
ቴሌቪዥን ይቅርታ እንዲጠይቅ የጠየቀበት ደብዳቤ
|


0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን