አሜሪካ የሶሪያ ወታደሮች ወደ ማንቢጅ ከተማ ገብተዋል መባሉ ስህተት ነው አለች



ከተማዋ በቱርክ ወታደሮች ከመያዟ በፊት የሶሪያ ወታደሮች ገብተው ባንዲራቸውን አውለብልበዋል መባሉ ትክክል አይደለም ብላለች፡፡

በእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ላለፉት 7ዓመት ከ9 ወራት የጦር ቀጣና የሆነችው ሶሪያ በተለይ የኃያለን ሃገራት ጎራ የያዘ ጣልቃ ገብነት ሃገሪቱን ብዙ መስዋእት አስከፍሏታል፡፡ ከ4መቶ ሺህ በላይ ሶሪያውያን ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከ6 ሚልየን በላይ የሚሆኑት ከመኖሪያ ስፍራቸው ወደ ሌላ ስፍራ ተፈናቅለዋል፡፡ 5 ሚልዮኖቹ ደግሞ ኑሯቸውን በስደት እንዲያደርጉ እና የውጭ እርዳታ እንዲጠብቁ ተገድደዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተወሰኑ የሶሪያ አካባቢዎች ከጦር ቀጣናነት ነፃ መውጣታቸውን ተከትሎ አሜሪካ በሃገሪቱ የሚገኙ ወታደሮቿን ሙሉ ለሙሉ አስወጣለሁ ማለቷ ሌላ ስጋትን ፈጥሯል፡፡
  

በሶሪያ 2ሺህ የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ስፍራዎች መካከል ደግሞ ማንቢጅ አንዷ ነች፡፡ በዚች ስፍራ የበላይነትን ለመያዝ የኩርድ እና የቱርክ ወታደሮች ሲፋለሙ ቆይተዋል፡፡

አሁን ላይ የሶሪያ ቁልፍ ከተማ በሆነችው ማንቢጅ የሶሪያ ወታደሮች ባንድራቸውን አውለብልበዋል መባሉን አዲስ ውጥረት እንዲፈጠር እያደረገ ነው፡፡
የሶሪያ ወታደሮች ከስድስት ዓመታት በኋላ ወደ ከተማዋ መግባታቸውን የጦሩ ቃላቀባይ ይፋ ማድረጉን በቢሲ ዘግቧል፡፡

አልጀዚራ በአንፃሩ የሶሪያ ወታደሮች ወደ ማንቢጅ ከተማ ገብተዋል መባሉ ሃሰት እና ባንዲራቸውንም እንዳልሰቀሉ የአሜሪካ ጦር ተናግሯል ብሏል፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋር በበኩሉ ወታደሮቹ ገብተዋል መባሉ ማረጋገጫ የሌለው ፕሮፓጋንዳ መሆኑ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ደግሞ አይ 24 ነው፡፡

በሌላ በኩል የቱርክ ወታደሮች ወደ ሶሪያ መግባታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች በስፍራው መታየታቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡


Post a Comment

0 Comments