አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘገበ
አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘገበ።
እንደ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘገባ ከሆነ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በቁጥጥር ስር የዋሉት በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ብክነት ፈጽመዋል በመባል ተጥርጥረው ነው።
በቀድሞ ስሙ ብአዴን እና የአሁኑ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንን እና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደው ነበር።
ነሐሴ 18/2010 . ነበር የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንን እና አቶ ታደሰ ካሳን ከማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱ ያስታወቀው።
ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች አንዱ የነበሩት አቶ በረከት የቀድሞ የማስታወቂያ ሚንስትር እና በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።


ምንጭ 
አማራ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ እና ቢቢሲ

Post a Comment

0 Comments