ገቢው በአጭር የፅሑፍ መልእክት በተዘጋጀ እጣ አማካኝነት ከደንበኞቹ የተሰበሰበ መሆኑን እና ገንዘቡን ለመሰብሰብ ሶስት ዓመት እንደወሰደበት የተቋሙ ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ገልፀዋል::
ወይዘሪት ፍሬሕይወት እንዳሉት ላለፉት 3 ዓመታት ለሜቄዶንያ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አማካኝነት ከህብረተሰቡ የሰበሰብነውን 74,718,165 (ሰባ አራት ሚልዮን ሰባት መቶ አስራ ስምንት ሺህ መቶ ስድሳ አምስት) ብር በደንበኞቻችን ስም ለማዕከሉ ገቢ ተደርጓል፡፡
ተቋሙ ከተለያዩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ጋር በመተባበር እና በተቋሙ ስም ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በሚልካቸው አጫጭር
መልእክቶች አመካኝነት ያለ ደንበኞቹ ፈቃድ ገንዘብ ይቆርጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ባካሄደው ‹ለውጥ› የታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን