ሩሲያ እና ቁልፍ አጋሮቿ ካቬንዚዌላው ፕሬዚዳንት ማዱሮ ጎን እንደሚቆሙ ገልፀዋል


ሩሲያ ፕሬዚዳንቱን በሃይል ከስልጣን ለማውረድ መሞከር ህገ ወጥነት ነው ብላለች 

ቻይና በበኩሏ በውጭ የሚጣል ማእቀብ እና ጣልቃ ገብነት ሁኔታዎችን ይበላጥ ያወሳስባል ብላለች፡፡


በሩሲያ እና በቻይና የሚመሩት የሃገራቱ ቁልፍ አጋሮች አሜሪካ በቬንዚዌላ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፎካካሪዎቹ መሪ ጁአን ጉይዶ ስልጣን እንዲይዙ የምታደርገው የውጭ ጣልቃ ገብነት ልታቆም ይገባል ብለዋል፡፡

ሩሲያ ትናንት ይፋ ባደረገችው ጠንከር ያለ አዋጅ ላይ ፕሬዝዳንት ማዱሮ ጎን መሆኗን ገልፃ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በቬንዚዌላ ላይ ‹‹መቅሰፍትን›› የሚያወርድ ነው ብላለች፡፡

የሩሲያው ምክትል የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ርያብኮቭ አሜሪካ ጣልቃ እንዳትገባ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሃገሪቱ ጣልቀ ከገባች በላቲን አሜሪካ ጥሩ የልማት ማሳያ የሆነችው ቬንዚዌላን ታናጋታለች ብለዋል፡፡

ሩሲያ ከስልታዊ አጋሯ ቬንዚዌላ ጎን ነች፣ ወዳጅነታችነን አጠናክረን ድጋፋችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡

የላቲን አሜሪካዊቷ ቬንዚዌላ ዋነኛ አጋር ሩሲያ በቢልዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ በድጋፍ እና በብድር መልክ ደግፋታለች፡፡

ባለፈው ታህሳስ ወርም ቲ ዩ 160 የተባሉ ሁለት የኒውክሌር ቦምቦችን በድጋፍ መልክ ሰጥታታለች፡፡

የሩሲያ ታችኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ ላይ ተፎካካሪው ጓይዶ ስልጣን ለመያዝ የሚያደርጉት ሙከራ ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡

ቻይና በበኩሏ ቬንዚዌላ ሉአላዊነት እንዲከበር እና የተረጋጋች ሃገር እንድትሆን መንግስትን እደግፋለሁ ስትል በተመሳሳይ ሐሙስ እለት ገልፃለች፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንዪንግ በእለቱ(ሐሙስ) በቤጂንግ በሰጡት መግለጫ ላይ በውጭ የሚጣሉ ማእቀቦች እና ጣልቃ ገብነቶች ሁኔታዎችን ከማወሳሰብ ውጭ ምንም አይነት መፍትሔ እንደማያመጡ አፅንኦት እንዲሰጥበት እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቬንዚዌላ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በ72 ሰዓታት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ፕሬዝዳንቷ አዘዋል፡፡
ዘገባው የዘጋርዲያን ነው፡፡

Post a Comment

0 Comments