ምሁራኑ በሱዳን እና በአልጀሪያ
የተነሱት ህዝባዊ ተቃውሞዎች አቢዮቱ መጀመሩን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል፡፡
በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2010 በቱኒዝያ
ጠንከር ያለ ፀረ መንግስት ተቃውሞ ተነሳ፡፡ ከዚያም ግብፅን፣ ሊብያን፣ የመንን፣ ሶሪያን እና ባህሬይንን በማዳረስ ''የአረብ አብዮት'' የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡
ተቃውሞው እያየለ ሄዶ ወደ እርስ
በእርስ ግጭት ተቀየረ በዚህም በርካቶች ህይወታቸው አጡ፣ብዙሃኑም ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው፣ መሪዎችም መንበረ ስልጣናቸውን በጉልበት
አጡ፡፡
ይህ ከሆነ ከዘጠኝ አመታት በኋላ
ይህው የአረብ አብዮት ድጋሚ ሊነሳ ይችላል ሲሉ የግብፅ ምሁራን እና ጋዜጠኞች ተንብየዋል፡፡
ምሁራን እና ጋዜጠኞቹ በሱዳን እና
በአልጀሪያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደ ምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡
በተለይም በሁለቱም ሃገራት ላይ
የተነሳው ተቃውሞ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እና በተለያዩ ድረገፆች መዛመቱ አብዮቱ እንዲነሳ ያደርጋል ሲሉ ከመጀመሪያው የአረብ
አብዮት ጋር በማመሳከር ገልፀዋል፡፡
ጅማሬው በተለይ እንደግብፅ
ላሉ የህዝባቸውን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የከለከሉ እና በሃገራቸው ላይ ያለውን ሰፊ ቀውስ እንዲሸፋፈን ለሚያደርጉ ሃገራት
ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው ብለዋል ምሁራኑ፡፡
የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር
የሆኑት ሃሰን ናፋ ሁለተኛው የአረብ አብዮት በሱዳን የተጀመረ ይመስላል፡ አልጀሪያም ለተመሳሳይ እጣ ተዘጋጅታለች ሌሎቹም መከተላቸው
አይቀርም ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡
ፕሮፌሰሩ አክለውም የአረቡ
ህዝብ ለአምባገነኖች እንደማይገዛ እና ማህበራዊ ኢ ፍትሃዊነትን እንደማይታገስ ግልፅ ነው ብለዋል፡፡
የሙስሊም ወንድማማቾች ተወካይ ቁጡብ
አል አረቢ በበኩሉ ‹‹የአረቡ አቢዮት ነበልባል አሁንም አለ ዘንድሮ ይበልጥ የሚዛመትበት ጊዜ ላይ ነው›› ብሏል፡፡
አልጀሪያውያን ተነስተዋል፡፡ በአረቡ
ህዝብ ላይ ምንም ብትዝቱም ልታቆሙት አትችሉም ህዝቡ ነፃነቱን ያውጃል ያሉት ደግሞ ገጣሚ አብዱላ ራሂም የሱፍ ናቸው ብሏል ሚድል
ኢስት ሞኒተር፡፡
ግብፃዊው የአልጀዚራ ጋዜጠኛ መሃመድ
ማኸር አክል በበኩሉ በሱዳን እና በአልጀሪያ የተነሳው ተቃውሞ ከባድ መሆኑን በመግጽ ለነፃነት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን