ሁለቱም መሪዎች በዋናነት በሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር መርሃ ግብር ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል
ቀደም ሲል ሰሜን ኮሪያ በምታበለፀገው ባስወነጨፈቻቸው ኒውክሌሮች ምክንያት
የኮሪያ ልሳነ ምድር ውጥረት ውስጥ ቆይቷል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚያስተለልፉት ፀብ አጫሪ
ማስጠንቀቂያዎች ደግሞ የሃገራቱን ውጥረት እንዲከር አድርጎት ቆይታል፡፡
ምንም እንኳን የተባበሩት መንግስታትን ድርጅትን ጨምሮ የሌሎች ሃገራት መሪዎች
አሜሪካ ፀብ አጫሪ መልእክቷን አንድታቆም ቢወተውቱም ጉዳዩ ግን እየጦፈ ሄዶ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ስጋት ውስጥ ከትቶት
ቆይቷል፡፡
የኋላ ኋላ ሰሜን ኮሪያ በሯን ለውይይት ክፍት ማድረጓን ተከትሎ ስጋቱን
አብርዶታል፡፡
የበላይነታቸውን ለማስመስከር ሲዛዛቱ የከረሙት ሁለቱ መሪዎችም ፀብ
አጫሪነታቸውን ትተው ውይይትን መርጠዋል፡፡
ከዛሬ ስምንት ወር በፊት ታሪካዊ ውይይታቸውን በሲንጋፖር ያካሄዱት ሁለቱም
መሪዎች ለሁለተኛ ዙር ውይይት በቬትናሟ መዲና ሃኖይ ተገናኝተዋል፡፡
ቀድሞ ንትርክ ላይ የነበሩት ሁለቱም መሪዎች ዛሬ ሃኖይ ሲገናኙ ደስተኞች
መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ኪም ጆንግ ኡን ታላቅ መሪ ነው ካሉ በኃላ ሰሜን ከሪያ
በተለይም በምጣኔ ሃብት ዘርፍ ታላቅ ተስፋ ያላት ሃገር መሆኗን ነግረዋቸዋል፡፡
‹‹ኪምን በማግኘቴ እና በጋራ በመሆናችን ክብር ይሰማኛል፡፡ የመጀመሪያው
ውይየታችን እጅግ ስኬታማ በሆነ መልኩ አካሂደናል፡፡ በጋራ እያካሄድን ባለው ተግባር ደስተኛ ነኝ፡፡ ያሁኑ ውይይትም ከባለፈው
ይበልጥ ስኬታማ ይሆናል ብዬ እጠብቃለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንዳልኩት ሃገሮ በተለይም በምጣኔ ሃብት ዘርፍ ያልተገደበ
ተስፋ ያላት ሃገር ናት፡፡ እርሶም ከሃገሮ ጋር ትልቅ ትልቅ ተስፋ አላችሁ፡፡ ስኬታማ እንድትሆኑም ድጋፍ እናደርጋለን›› ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል
ኪም ጆንግ ኡን በበኩላቸው ሁሉንም መሰናክሎችን አልፈን ለዛሬ በቅተናል ሲሉም
ተደምጠዋል፡፡
ሁለቱም መሪዎች በዋናነት በሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር መርሃ ግብር ዙሪያ ይወያያሉ
ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ውይይታቸው ልክ እንደመጀመሪያው ስኬታማ እንደሚሆንም ተስፋቸውን ተናግረዋል፡፡
ቢቢሲ እና ሲኤን ኤን

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን