‹‹የተዳፈነዉ የአንበሳ አውቶቡስ የሙስና ወንጀል››
በ1935 ዓ.ም በዝቅተኛ ክፍያ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በአክሲዮን ማህበርነት ተቋቋመ - የያኔው የኢትዮጵያ ተሸከርካሪ መኪናዎች ድርጅት የአሁኑ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት፡፡
አሁን ድርጅቱ ታሪክ ብቻ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ለምን?
የፌደራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በድርጅቱ ውስጥ ስለተፈፀመው የሙስና ተግባር ለማጣራት በ2007 ዓ.ም ጥናት አካሄደ፡፡
በጥናቱም በአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ላይ ለስርቆት፣ ለብልሽት እና ድርጅቱን ለውድቀት የሚዳርጉ የአሰራር ክፍተቶች መከናወናቸውን አግኝቷል፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ
‹‹የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሙስና ወንጀል ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ ፖሊስ የተጀመረው ምርመራ አመልካቹ ይሁኑ ሌላ አካል ያቀረቡት ጥቆማ ለመሆኑ አጣርቶ ባልገለፀበት ሁኔታ ምርመራውን አላጣራም ብሎ መዝገቡን መመለሱ ቅንነት እና ግልፅነት የጎደለው አካሄድ መሆኑን ተገንዝበናል››
ሲል ህዳር በፃፈው የውስጥ ማስታወቂያ ላይ ተመልክተናል፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይህን ይበል እንጂ ጉዳዩ ምርመራ ተደርጎበት ለህግ እንዲቀርብ አላደረገም!!!
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን