ቦይንግ 737 ማክስ 8 ከተባለው አውሮፕላን ጋር በተያያዘ አደጋ ሲከሰት ባለፉት ስድስት ወራት ይህ ሁለተኛው ነው።
የንግድ በረራ የሚያካሂዱ የኢትዮጵያ የቻይና የኢንዶኔዢያ እና የካይሜን አየር መንገዶች አውሮፕላኑን መጠቀም አይችሉም ተብሏል።
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር
መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላኑ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው እሁድ ጠዋት 2፡38 ሲሆን ከ6 ደቂቃ በኋላ ከአብራሪዎቹ ጋር ይደረግ የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ ከደቂቃዎች በኋላ ቢሾፍቱ አካባቢ መከስከሱን ነው የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ
አቶ ተወልደ ገብረማርያም የተናገሩት ።
የአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ቦይንግ በበኩሉ በተፈጠረው አደጋ እጅግ ማዘኑን በመግለጽ የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጥና የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት በሚደረገው ስራ ላይ እርዳታ የሚሰጥ ቡድን እንደሚልክ አስታውቋል።
የምርመራ ሂደቱም የሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መስሪያ ቤቶች ከቦይንግ ባለሙያዎችና ከአሜሪካ የትራንስፖርት ደህንነት መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር የሚካሄድ ነውም ተብሏል።
ባለፈው ጥቅምት ''የላየን'' አየር መንገድ ንብረት የሆነ ተመሳሳይ አውሮፕላን ተከስክሶ 189 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
በትናንትናው ዕለት በቦይንግ 737 በረራ ቁጥር ET302 የ157 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው አሰቃቂ አደጋ የ33 ሃገራት ዜጎች እንደነበሩበት ይታወሳል፡፡
የቻይና አየር መንገዶች የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላንን መጠቀም የሚችሉት የኤቪዬሽን መስሪያ ቤቱ ወደፊት በሚሰጠው መግለጫ መሰረት እንደሆነ አስታውቋል።
![]() |
የኢትዮጵያ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ስባሪ
|




0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን