![]() |
| አቶ ተፈራ ዋልዋ: የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የበላይ ጠባቂ |
ኢትዮጵያ በመጪው ህዳር ወር ሳተላይት እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ ተናገሩ፡፡
የበላይ
ጠባቂው እንዳሉት ሳተላይቱ ከመጠቀ በኋላ በተለይም በግብርና እና በመረጃ ልውውጥ ዘርፍ ከፈተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ሳትላይቶችን
ወደ ህዋ ያመጠቁ ሃገራት ከዘርፉ በሚያገኙት ገቢ ምጣኔ ሃብታቸው ማደጉን የገለፁት አቶ ተፈራ ኢትዮጵያም ሳተላይቷን ካመጠቀች ለዚሁ
አገልግሎት የምታወጣውን ወጪ ያስቀርላታል ብለዋል፡፡
የመጀመሪያው
ሳተላይት የሚመጥቀው በቻይና ሲሆን በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ደግሞ የሳተላይት ሙሉ ስራ ኢትዮጵያ ውስጥ ይከናወናል ብለዋል፡፡
ተቋሙ በዚሁ ዘርፈ ላይ የሚያገለግሉ መሃንዲሶችንና ሳይንቲስቶችን ማብቃቱን ገልፀዋል፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን