የሱዳኑ እስላማዊ ፖፑላር ፓርቲ ስምምነት የተደረሰበት የጥምር ምክርቤት ማቋቋሚያ መርህ አልቀበልም ብሏል፡፡



ፓርቲው ይህን ያለው የሽግግር መንግስቱን የሚመራ ጥምር ምክርቤት ማቋቋሚያ መርህ ይፋ፡፡

ሱዳንን ለ30 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሯት ኦማር አልበሽር በህዝቡ የበዛ ተቃውሞ እና በወታደራዊ ኃይል አማካኝነት ከስልጣን ከተወገዱ ጀምሮ ሃገሪቱ እየተመራች ያለችው በወታደራዊ ኃይል ነው፡፡ ለሁለት ዓመታትም በዚሁ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት እየተመራች እንደምትቆይም መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ይህ ደግሞ ለሱዳናውያኑ የሚዋጥ ውሳኔ አልሆነም፡፡ ስልጣኑ በፍጥነት ወደ ሲቪል ሊተላላፍ ይገባል፤ ሱዳን በወታደራዊ ኃይል መመራት የለባትም ሲሉም በሃገሪቱ የጦር ቢሮ ፊት ለፊት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ማሰማት ቀጥለዋል፡፡
የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት አባላት ከሁለት ሳምንታት በፊት አዲስ አበባ በሚገኘው የሱዳን ኤምባሲ በመገኘት የሽግግር ጊዜው ሁለት ዓመት እንዲሆን የተወሰነው በቂ ጊዜ ተወስዶ የተሳካ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ነው ሲል መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
የህዝቡ ተቃውሞ መቀጠሉን ተከትሎ ደግሞ ቅዳሜ እለት ወታደራዊ መንግስቱ እና ተቃዋሚ ቡድን በጋራ ባካሄዱት የመጀመሪያ መደበኛ ውይይት የሽግግር መንግስቱን የሚመራ ጥምር ምክርቤት ማቋቋሚያ መርህ በማውጣት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በአንፃሩ የሱዳኑ እስላማዊ ፖፑላር ፓርቲ ፒሲፒ ስምምነት የተደረሰበት የጥምር ምክርቤት ማቋቋሚያ መርህ አልቀበልም ብሏል፡፡
የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አሊ አል ሃጂ ‹‹እኛ ያልተሳተፍንበትን ስምምነት አንቀበልም፤ ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎችን ያገለለ ስምምነት ልንቀበል አንችልም፡፡›› ብለዋል፡፡
በመከላከያ ካውንስል እና ዲክላሬሽን ኦፍ ፈሪደም ኤንድ ቼንጅ (DFC) መካከል በተካሄደው አግላይ ስምምነት ላይ ሶስት እስላማዊ ጀነራሎች እንደይሳተፉ ተደርገዋል ያሉት ዋና ፀሐፊው ማንም የፖለቲካ ፓረቲ በወታደራዊ ካውንስሉ ላይ ምንም አይነት እቅድ እንዲፈፀምለት የማድረግ መብት የለውም ማለታቸውን ሮይተርስ እና ሱዳን ትሪቡን ዘግበዋል፡፡



  

Post a Comment

0 Comments