በመጨረሻም ኦማር አልበሽር ከ30
ዓመት በኋላ ስልጣን ማስረከባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
·
ሱዳን የዳቦ እና የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ
ተቃውሞ እያደር ኦማር አልበሽር ስልጣን ይልቀቁ ወደሚል ከረር ያለ ተቃውሞ ተቀይሮ ቆይቷል፤
·
ተቃውሞው ከ8 ቀናት በኋላ 5 ወር ይሞላዋል፡፡ በነዚህ ወራትም አብዛኞቹ የሃገሪቱ ዋና ዋና መንገዶች
በተቃዋሚዎች ተጨናንቀው ቆይተዋል
·
የሃገሪቱ ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቀሽ ጭስ ሲጠቀም ቆይቷል፡፡
·
እየበረታ የሄደው ተቃውሞ መልኩን በመቀየሩ የሃገሪቱ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል፤ ቢሆንም ግን
ተቃውሞውን ሊገታ አልቻለም፡፡
·
ጋዜጠኞች በማይታወቅ ስፍራ ታስረዋል፤ ሁለት በዓረቢኛ ቋንቋ የሚሰሩ የዜና ጣቢያዎችም ፈቃዳቸው ተሰርዞ
በሃገሪቱ እንዳይሰሩ ተከልክለዋል፡፡
·
የሱዳን መንግስት በዚሁ ምክንያት 31 ሰዎች መገደላቸውን ሲገልፅ human rights watch ደግሞ
51 ሰዎች ተገድለዋል ብሏል፡፡
·
የኋላ ኋላ የ75 ዓመቱ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽር ከህዝቡ ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር
ህዝቡ ግን አልተቀበላቸውም፡፡
·
በመጨረሻም ኦማር አልበሽር ከ30 ዓመት በኋላ ዛሬ ስልጣን አስረክበዋል፡፡
·
የፈረንጆቹ 2019 ዓመት ከገባ ወዲህ የቀድሞው የአልጀሪያው ፕሬዝደንት አብዱላዚዝ ቡቶፍሊካን ተከትለው
በህዝባዊ ተቃውሞ ስልጣን ያስረከቡ በአፍሪካ ሁለተኛው መሪ ናቸው፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን