እረፉ! .*** በረከት በላይነህ*** ከእያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ቲያትር የተወሰደ|#AS_production

እረፉ!
“ዘመመ” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ
እረፍ!
ቆሜያለሁ ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘና ቆዳዬን አትግፈፍ፡፡
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየ አልጋህ እደር በየ እንቅልፍህ አልም
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ፡፡
ማን እንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ፡፡
ምክንያት ታመመ መፍትሔ ታመመ
ከጥያቄው በፊት መልሱ እየቀደመ
ሌብነት ገነነ
ግርግር ገነነ
ብልጭልጭ ገነነ
ኪሳራ ገነነ
ደላሎች ገነኑ፣ደላሎች ጀገኑ
ባልዋለ ገበያ ዋጋ እየተመኑ!
.
.*** በረከት በላይነህ***
ከእያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ቲያትር የተወሰደ

Post a Comment

0 Comments