በሃገሪቱ
ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ቀጥሎ ሰኞ እለት ከስድስት በላይ ሰዎች ሲገደሉ 100 የሚጠጉ ደግሞ ተጎድተዋል፡፡
ይህን
ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃገሪቱ ወታደር በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ ተጠቅሟል ሲል ምክር ቤቱን ወንጅሏል፡፡
የዋጋ
ንረት ለተቃውሞ አደባባይ ላይ ካወጣቸው የአፍሪካ ሃገራት መካከል አንዷ ናት ጎረቤት ሃገር ሱዳን፡፡
በዳቦ
እና በነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት በተለያዩ ዓመታት ተቀውሟቸውን ሲያሰሙ የቆዩት ሱዳናውያኑ ልክ የዛሬ ስድስት ወር የጀመሩት ተመሳሳይ
ተቃውሞ ግን ከወትሮው የተለየ ክስተት አስተናግዷል፡፡
የኋላ
ኋላ መልኩን ወደ ፖለቲካ የቀየረው ይህው ህዝባዊ ተቃውሞ የበርካቶችን ህይወት ካስገበረ በኋላ ፕሬዝዳን ኦማር አልበሽር ከህዝቡ
ጋር ለመወያየት ቢማፀኑም ሰሚ አጥተዋል፡፡ የ30 ዓመት መንበረ ስልጣናቸውን ተነፍገው ወደ ወህኒ ተወስደዋል፡፡
ይህ ድርጊት
አንዱ እቅዳቸው ቢሆንም ሃገሪቱን በጊዜአዊነት የሚያስተዳድራት ወታደራዊ ምክር ቤቱ ስልጣኑን ለህዝባዊ መንግስት እስኪያስረክብ ድረስ
ተቃውሟችንን አናቆምም በማለት ውሎ አዳራቸውን አደባባይ አድርገዋል፡፡
አንዴ
ሰላማዊ አንዴ ደግሞ የሰው ህይወት እያስገበረ የሚገኘው ይህው ተቃውሞ ሰሞኑን በሃገሪቱ ወታደራዊ መንግስት እና በህዝቦች መካከል
የተፈጠረወን ቁርሾ አንሮታል፡፡
በተለይም
ከ10 ቀናት በፊት በሽግግር ምክርቤቱ እና በተቃዋሚ ቡድን መሪዎች መካከል የተደረገው ውይይት ሳያስማማቸው በመቅረቱ የሱዳን ተፎካካሪ
ቡድን ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲኖር ጥሪ አቀርባለሁ በማለቱ ባለፈው ሰኞ ከስድስት በላይ ሰዎች በወታደር ተገድለው 100 የሚጠጉ
ደግሞ መጎዳታቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡
ድርጊቱን
ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሃገሪቱ ወታደር በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ ተጠቅሟል ሲል
ምክር ቤቱን ወንጅሏል፡፡
ግቤ በሱዳን
እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲተገበር ነው ያለው የሃገሪቱ ወታደራዊ የሽግግር ምክርቤት ዴሞክራሲ መወያየት ነው ያን ማድረግ እንፈልጋለን
ሲል ትናንት ጥሪ አቅርቧል፡፡
በመሆኑም
ምክርቤቱ ከተቃዋሚ ቡድን መሪዎች ጋር እወያያለሁ ሲል ቀጠሮ ይዟል፡፡
ባለፈው
ሳምንት ከተፎካካሪ ቡድኖች ጋር ተወያይቶ በተለይም ከዲክላሪሽን ኦፍ ፍሪደም አንድ ቼንጅ ፓርቲ ጋር በቁልፍ ጉዳዮች ሳይስማማ የቀረው
ምክርቤቱ በሚያካሂደው ውይይት ይስማሙ ይሆን? ጊዜ ይመልሰው፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን