‹‹ኢትዮጵያን ጠልቼ ነበር፤ የሰው ብርታት ግን ሃገሬን እንድወድ አድርጎኛል፡፡›› ወ/ሮ መሳይ ነጋሽ
እሁድ እለት፤ የሁለት አዳጊ ህፃናት እናት የሆኑትን፤ ጎረቤት ከሚሰጣቸው የእለት ኩርማን ውጭ ምንም ዓይነት ገቢ ወደ ሌላቸው ወደ ወ/ሮ መሳይ ነጋሽ ደሳሳ መጠለያ ጎራ ብዬ ነበር፡፡
የተጠለሉባት ደሳሳ ‹‹ቤት›› ጣራዋና ግድግዳዋ ላይ የበዛ ክፍተት በመኖሩ አረፍ የሚሉባት ‹‹ፍራሽ›› እና ማንደጃቸው ተሰብሰበው ጥግ ይዘዋል፡፡
ክረምቱን የሚያልፉበት ላስቲክ በአንዱ ግድግዳ በኩል ተለጥፎ ነበር፡፡ ጣራው አሁንም ክፍተቱን እንደጠበቀ ነው፡፡
ምን መስራት እንዳለባቸው ትንሽ ካወጋን በኋላ ፊዮሪ አብርሃ Fiori Abraha የተባለች እህት የላከችላቸውን ገንዘብ ከፊሉን ስሰጣቸው ማመን እያቃታቸው ተቀበሉኝ፡፡
በድህነት ምክንያት ኢትዮጵያን ጠልተው ነበር፤ አሁን ደግሞ ወድደዋታል፡፡
የመጀመሪያ ድጋፍ ላደረገችላቸው በስዊድን ለምትገኘው ተማሪ ለፊዮሪ ይህን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን