አበባው መላኩ እንዲህ ያደርገኛል| ENDIH YADERGEGNAL Abebaw Melaku |#AS_production |...


እንዲህ ያደርገኛል

እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ እለት እንዲህ ያደርገኛል!
ሰዉነቴ ሁሉ ጆሮ ይሆንና
የብናኝ ኮሽታ ገዝፎ ይሰማኛል
ኮቴ እንደ መብረቅ እንዳንዳች ፍንዳታ የጆሮዬን ታንቡር ደርሶ ይጠልዘኛል
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ እለት እንዲህ
ያደርገኛል

ጥሞናዬ ረቆ መንፈሴን አምጥቆ የሷን ኮቴ ናፍቆ
የፍቅሬን አካሄድ የሰበር ሰካዋን ከእርምጃዎች ሁሉ ከዳናዎች አዉቆ
በናፍቆቷ ደጋን በጉጉት ፍላፃ ተወጥሮ ከሮ
ጅስሜ እንደ አሞራ እንደ ብርቱ ንስር ክንፍ አዉጥቶ በሮ
ምድርና ሞላዋን አለምን ይቃኛል
ከፍቅሬ በስተቀር ሁሉ ከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ይለኛል
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ እለት እንዲህ
ያደርገኛል
በፍቅሯ ልእልና በፍቅር ፅናቴ
ከመንደሬ ገዳም ከጎጆ በአቴ
ከመልአክት ረቅቄ ከፃድቅ ፀድቄ
እጠብቃታለሁ
እመጣለሁ ብላኝ መች ተኝቼ አዉቃለሁ
አለም ጊዜ ፀሃይ ሁሉም ቀጥ ብለዉ
የኪዳኔን ታቦት ፅላቴን አክብረዉ
ይማፀኑልኛል ይማልዱልኛል
ይህ ሚስኪን ፃድቅ ሰዉ
ከአለም የመነነዉ ባአቱን የዘጋዉ
ፀሃይን አስቁሞ ጊዜን የገዘተዉ
እንመጣለሁ ብለሽ እንዳትዘገይ ነዉ
እንዳትቀሪበት ነዉ
ብለዉ ይሉልኛል 
ጨረቃ ክዋክብት ይማልዱልኛል
የፍቅር ብርታቴን ሁሉም ያዉቁልኛል
ከአይን ያዉጣህ ካይን ያዉጣህ ካይን ያዉጣህ ይሉኛል
አንዳንዴም ሽዉ ሲል እንዲህ እሆናለሁ
ከቤቴ ቁጭ ብዬ በሃሳብ እመጥቃለሁ
እሳን እየጠበኩ እፈላሰማለሁ 
እላለሁ
ይህ ሁሉ ጥሞና ይህ ሁሉ ትጋት
ለሌላም ለሌላም ቢሆን ምን አለበት
አዬ ጊዜ ደጉ አዬ ወጣትነት
እላለሁ
እድሜ ለሷ ፍቅር መንፈሴን አድቅቆ ልቤን ለሚገዛዉ
በሌላማ ጊዜ በጥልቅ ለመመሰጥ አእምሮዬን ባዘዉ
መች እሺ ይለኛል መች እሺ እላለሁ
………….አበባው መላኩ…………

Post a Comment

0 Comments