የአፍሪካ ህብረት በሱዳን የስልጣን ሽግግር ሂደት ላይ ውይይት ሊያደርግ ነው፡፡



አምስት ወራትን ያስቆጠረው የሱዳናውያኑ ተቃውሞ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

አዲሲቷ ሱዳንን ለመገንባት ተስፋ የሰነቁ ሱዳናውያን የሌሊት ቁር እና የቀን ሃሩር አቧራ ታክሎበት ቢፈራረቅባቸውም ተስፋቸውን ግን ሊያጨልመው ተስኖታል ይላል የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ፡፡

የኑሮ ውድነት ለተቃውሞ አደባባይ ያስወጣቸው ሱዳናውያኑ 30 ዓመታትን የመሯቸው የቀድሞውፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽርን ካስወገዱ በኋላም ህዝባዊ መንግስት ስልጣኑን እስካልተረከበ ድረስ ከአደባባይ ንቅንቅ አንልም በማለት ውሎ አዳራቸውን አደባባይ አድርገዋል፡፡

ስልጣኑ በፍጥነት ወደ ሲቪል ሊተላላፍ ይገባል፤ ሱዳን በወታደራዊ ኃይል መመራት የለባትም ሲሉም በሃገሪቱ የጦር ቢሮ ፊት ለፊት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ማሰማት ቀጥለዋል፡፡

የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት አባላት ከሶስት ሳምንታት በፊት አዲስ አበባ በሚገኘው የሱዳን ኤምባሲ በመገኘት የሽግግር ጊዜው ሁለት ዓመት እንዲሆን የተወሰነው በቂ ጊዜ ተወስዶ የተሳካ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ነው ሲል መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል ቢሆንም ግን ሱዳናውያኑ ሊቀበሉት አልቻሉም፡፡

ይህን ተከትሎም የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ስልጣኑን ለህዝባዊ መንግስት እንዲያስረክብ የ60 ቀናት የጊዜ ገደብ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የህብረቱ የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት በሱዳን የስልጣን ሽግግር ሂደት ላይ ውይይት ሊያደርግ መሆኑን በሱዳን የአፍረሪካ ህብረት አዲሱ ልዩ መልእክተኛ መሃመድ አል ሃሰን ለበት ገልፀዋል፡፡

ልዩ መልእክተኛው በሱዳን መዲና ካርቱም ከሱዳን ባለስልጣናት፤ከአውሮፓ እና አፍሪካ ህብረት ጥምር ዘመቻ በዳርፉር ሃላፊዎች እንዲሁም ከውጭ ዲፕሎማቶች ጋር መወያየታቸውንም ነው የገለፁት፡፡

የሱዳን ወታደር እና ተቃዋሚዎች የስልጣን ሽግግር ሂደትን በተመለከተ የደረሱበትን ደረጃ ለመመልከት ህብረቱ ውይይት ሊያደርግ ነው መሆኑን የዘገበው ሱዳን ትሪቡን ነው፡፡

ህብረቱ የሱዳን ወታደር ስልጣኑን ለህዝባዊ መንግስት እንዲያስረክብ የ60 ቀናት የጊዜ ገደብ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
    

ተዛማጅ ዘገባዎች


Post a Comment

0 Comments