የሱዳን ተፎካካሪ ቡድን ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲኖር ጥሪ አቀርባለሁ ሲል የሽግግር ምክር ቤቱን አስጠነቀቀ፡፡


ተፎካካሪ ቡድኖች እና ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ሳይስማሙ ቀርተዋል፡፡


አምስት ወራትን ያስቆጠረው የሱዳናውያኑ ተቃውሞ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
በትናንትናው እለት ወታደራዊ የሽግግር ምክርቤቱ  እና ተፎካካሪዎች በካርቱም ያደረጉት ውይይት ልዩነታቸውን ይበልጥ እንዲሰፋ ድርጎታል፡፡


የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክርቤት አባል ያሴር አታ በርካታ የፖለቲካ ቡድኖች በውይይቱ ተጋብዘው በርካታ እቅዶችን እንዳቀረቡ እና ውይይት እንደተደረገባቸው ገልፀዋል፡፡

‹‹177 እቅደችን ተቀብለን ግምገማ እና ጥናት አድርገንባቸዋል፡፡ አብዛኞቹ በሽግግሩ ዙሪያ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ እና ለድርድር እንዲቀረቡ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ከሽግግር ምክረ ቤቱ የፖለቲካ አባላት ጋር በሱዳን የተደረገው ውይይት በሽግግር ወቅት ስለሚኖረው የአስተዳደር ስልት ለይቶ ለማወቅ የሚረዳ ነው›› ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

የዲክላሪሽን ኦፍ ፍሪደም አንድ ቼንጅ ፓርቲ መሪ ማዳኒ ዓባስ ማዳኒ በበኩሉ ወታደራዊ ምክር ቤቱ ጉዳዮችን በመለጠጥ ስልጣን ወደ ህዝበዊ መንግስት እንዳይቀየር እያጓተተ ነው ሲል ተችቷል፡፡

‹‹የሽግግር ምክር ቤቱ አቢዮታዊ አማራጮችን ለማስቀረት እየጣረ ነው፡፡ እንደ ሁልጊዜውም የድሮ ሂደቶችን በመከተል ስልጣን ከእጁ እንዳይወጣም እየጣረ ነው፡፡ ቀድሞ ስልጣን ላይ የመቆየት ፍላጎት የለኝም ያለው ምክር ቤቱ በአንፃሩ  ላይ ያ ሁሉ ወር ነገሮችን ቢሮክራሲያዊ እያደረገብን ነው፡፡›› ብሏል ዓባስ ማዳኒ

የዲክላሪሽን ኦፍ ፍሪደም አንድ ቼንጅ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ካሊድ ኦማር የሱፍ በበኩሉ ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ስልጣን ላለማስረከብ ጉዳዮችን እያጓተተ ነው እቅዳችንንም ውድድ እንዲሆን አድርጓል ብሏል፡፡ በመሆኑም ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲኖር ጥሪ አቀርባለሁ ሲል የሽግግር ምክር ቤቱን አስጠንቅቋል፡፡

‹‹ምንም እንኳን ማነሳሳት አላማችን ባይሆንም ተቃውሟችንን እንድንቀጥል እና የማቀጣጠል ተግባራችንን እንድናጠናክር ተስማምተናል፡፡ እስካሁን ድረስ አቢዮታችን ግቡን አላሳካም፤ ስልጣን ወደ ህዝባዊ መንግስት አልተሸገረም፤ የድሮ አሰራሮችም እስካሁን አልተሻሻሉም፡፡ የፀጥታ ኃይሉ ተግባር አሁንም እንደቀድሞው ነው፡፡ ለውጥ የለም፡፡›› ሲልም መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ዋና ፀሐፊው በርካታ አማራጮች እንዳሉ እና ከነዛም መካከል ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ፤ በየ አደባባዮቹ መቀመጥ እና ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲኖር ማድረግ ይጠቀሳሉ ብሏል፡፡

ምንጭ
አልጀዚራ እና አናዶሉ ኤጀንሲ


(AS ዘ ብሔረ ጦቢያ)


ተዛማጅ ዘገባዎች

Post a Comment

0 Comments