ዋና መቀመጫውን በአሜሪካ ቺካጎ ያደረገው ግብረሰዶማዊነትን ለማስፋፋት የሚጓዘው #ቶቶ ጉብኝት በኢትዮጵያ ቅዱሳት ገዳማት እና ታሪካዊ ቦታዎች ላይ የ16 ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ማቀዱን እየገለፀ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ግብረ ሰዶምነትን በይፋ የከለከለች ሃገር ብትሆንም ድርጅቱ ግን ጉብኝት ከማድረግ የሚያግደኝ አንዳች ነገር የለም ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት አባቶች በኩል ተቃውሞ የደረሰው የግብረሰዶማነት ጉዞ ኩባንያ ቶቶ፤ ጉዞውን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርግ ከሆነ ግድያ እንደሚፈፀምበት ዛቻ እንደደረሰው ገልጿል፡፡
‹‹ሃጢያትን እና ሰይጣናዊ ተግባራትን የሚከውነው ይህው ተቋም ዝም ሊባል አይገባም፤ መንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ሊቃወም ይገባል፡፡›› ሲሉም የሃይማኖት መሪዎች አስጠንቅቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተርስቲያን የሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት የቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እና ለሌሎች ተቋማት በላከው ደብዳቤ ሁነቱን ተከትሎ ለሚፈጠረው ችግር ቤተክርስቲያኒቱ ኃላፊነት እናደማትወስድ አስጠንቅቋል፡፡
ምንጭ AFP


0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን