በኬንያ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከአንድ ሚልዮን በላይ ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል፡፡




በተለይም በሰሜናዊ የኬንያ ክፍል የሚኖሩ አርብቶ አደሮች በድርቁ ምክንያትም ለስደት እና ለግጭት ተዳርገዋል፡፡

አና ሊሳንጅሬ በሰሜን ኬንያ በአርብቶ አደርነት የሚተዳደሩ ኬንያዊት ናቸው፡፡ በአካባቢያቸው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ግጦሽ እና ውሃ በመጥፋቱ  ከነቤተሰባቸው ለመሰደድ ተገድደዋል፡፡

ለሚያረቧቸው እንሰሳት የሚሆን ግጦሽና ዉሃ ለማግኘትም እንደተራቡ የአንድ ቀን ጉዞ ያደርጋሉ፡፡

‹‹እኛ በምንኖርበት አካባቢ ዝናብ የለም፡፡ ስለዚህ እንሰሶቻችን ሊኖሩ ወደሚችሉበት ስፍራ እየተሰደድን ነው፡፡›› አና ሊሳንጅሬ



በሰሜናዊው ኬንያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እረኞች ለከብቶቻቸው የሚሆን ግጦሽና ዉሃን ለማግኘትማራላል ወደተባለች አካባቢ እና ወደ ሌሉችም ስፍራዎች ይሰደዳሉ፡፡
በሃገሪቱ እየተከሰተ ባለው ተደጋጋሚ ድርቅ ምክንያትም በእረኞች እና በአካባቢው ተወላጆች መካከል ግጭቶች ይነሳሉ፡፡

እንደ የአልጀዚራዋ ካትሪን ሶል መረጃ በአካባቢው የሚነሱ ግጭቶች መንስኤያቸው ቀላል ቢሆንም የበርካቶችን ህይወት እስከመቅጠፍ ይደርሳል፡፡

እነዚህ በኬንያ ሳምቡሩ በተባለች ቦታ የሚኖሩ ሽማግሌዎችና የጎሳ አባላት ናቸው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት በተከሰተው ችግር ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት ፀብ እና መፍትሔ ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

ዶሚኒክ ሌሌሲት በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ግጭት ተነስቶ ወላጅ አባቱን አጥቷን፡፡ እሱም በጥይት ፍንጣሪ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

‹‹ፓኪዋ ላይ ድርቅ ሲከሰት እረኞች ወደዚህ ይመጣሉ፣ ሳምቡሩ ሲደርቅ ደግሞ ወደ ፖኮት እንሄዳለን፡፡ እነሱ ወደኛ ሲመጡ ከብቶቻችንን ይሰርቃሉ፡፡ እኛም ስንሄድ እንደዛው፡፡ በዚህ መሃል እንጋጫለን፡፡›› ዶሚኒክ ሌሌሲት

በኬንያ እንዲህ ዓይነቱ ድርቅ ተከስቶ ሚልየኖችን ለርሃብ ሲያጋልጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ሃገሪቱ የዛሬ ሁለት ዓመት በገጠማት ድርቅ ምክንያት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ማወጇ አይዘነጋም፡፡ 
አልጀዚራ ነው የዘገበው፡፡

Post a Comment

0 Comments