ከአንድ ሰዓት በፊት #በዶዶላ ስላለው ሁኔታ ለማጣራት ስልክ ደውዬ ነበር፡፡
በአካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች በግጭቱ ምክንያት ከ3ሺህ 6መቶ በላይ ተፈናቃዮቸች በሁለት አብያተ ክርስቲያናት (በገብረ ክርስቶስ እና በኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን) ተጠልለው በፌደራል ፖሊስ ጥበቃ ቢደረግላቸውም በረሃብና በውሃ ጥም በርካቶች ታመዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ በአብያተ ክርስቲያናቱ ከተጠለሉ ስምንት ቀናት ቢሆናቸውም እስካሁን አንድ ጊዜ ብቻ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ነግረውኛል፡፡

አርሶ አደሮቹ እንደነገሩኝ 1ቦቴ ውሃ፣ ለእያንዳንዳቸው 4ኪሎ ሩዝ እና አንዳንድ ብርድ ልብስ ቀርቦላቸዋል፡፡

አሁን ግን የምግብ ድጋፍ የሚያደርግላቸው ባለመኖሩ በረሃብ እየተሰቃዩ እንደሆነም ነው የነገሩኝ፡፡


የክርስትና እምነት ተከታዮች እየተለዩ እየተገደሉ መሆኑንም የአካባቢው ነዋሪ አርሶ አደር አሳውቀዉኛል፡፡

‹‹ቄሮ ጥቃት ሲፈፅምብን የክልሉ ልዩ ፖሊስ ቄሮን ሲደግፍ ነበር፡፡›› ሲሉም ነው የነገሩኝ፡፡
ከብቶቻቸው የት እንዳሉ እንደማያውቁ እና ቤት ንብረታቸው እንደተቃጠለም ነው ያሳወቁኝ፡፡

‹‹ምርታችንን መሰብሰበ አልቻልንም፤በከብቶችም እየተበላ ነው፡፡›› ሲሉ ነግረውኛል፡፡
የትኛውም የመንግስት ባለስልጣን ያለነንበትን ሁኔታ አላየልንም እባካችሁን ድረሱልን ሲሉም ተማፅነዋል፡፡

ስለ ድጋፉ ሁኔታ ለማወቅ በአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የሎጅስቲክስ ዳይሬክተር አቶ ሃይደሩስ ሃሰንን ጠይቄአቸው ለአንድ ወር የሚሆን የምግብ
ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ወደ ስፍራው ተልከዋል ብለውኛል፡፡
ነገ (ሐሙስ) ዶዶላ ይደርሳሉ ብለውኛል፡፡

Post a Comment

0 Comments