በኢራን በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት 106 ሰዎች መገደላቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ አደረገ፡፡



ተቃውሞው በ21 የሃገሪቱ ከተሞች ላይ እየተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

አርብ እለት የተጀመረው የኢራናውያን ተቃውሞ አሁንም ቀጥሎ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡
ሲቢሲ ኒውስ እንደዘገበው አሁን ላይ በኢራን ስራ ፈልጎ ማግኘት እጅግ ከባድ ነው፡፡ የኑሮ ውድነት፣ የሃገሪቱ ገነዘብ የመግዛት አቅም መዳከምና የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት መቀዛቀዝ ኢራናውያኑን ለተቃውሞ ጋብዟቸዋል፡፡
አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለቻቸው ማእቀቦች ደግሞ ለሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት መዳከምና ለዜጎቿ ጉስቁልና ምክንያቶች ናቸው፡፡
በሃገሪቱ 21 ከተሞች ላይ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት ዜጎች ሃሳባቸውን የሚለዋወጡበት የመገናኛ ዘዴ የሆነው ኢንተርኔት 90 በመቶ ተዘግቷል፡፡
አልጀዚራ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጠቅሶ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ በዓለም ከፍተኛ የነዳጅ አቅራቢ በሆነችው ኢራን ለቀናት በዘለቀው ተቃውሞ ምክንያት ከ100 በላይ ኢራናውያን ተገድለዋል፡፡ ዋነኛው ምክንያትም የነዳጅ ዋጋ በ200 በመቶ መጨመር መሆኑን በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
የኢራን የፀጥታ ሃይሎች በተቃዋሚዎች ላይ ያልተመጣጠነ ሃይል በመጠቀማቸው ተቃዋሚዎችን እየገደሉ ነው ሲልም አምነስቲ የፀጥታ ሃይሎችን ተጠያቂ አድርጓል፡፡
‹‹ከታማኝ ምንጭ ባገኘነው መረጃ መሰረት በሃገሪቱ 21 ከተሞች በተካሄዱ ተቃውሞዎች ምክንያት ቢያነስ 106 ሰዎች ተገድለዋል›› ሲል አምነስቲ አንተርናሽናል፡፡ የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት የሟቾች ቁጥር 200 ሊደርስ ይችላልም ሲል ገልጿል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የሰበዓዊ መብት ኤጀንሲ በበኩሉ በግጭቱ ምክንያት በርካቶች ህይወታቸውን እንዳጡ ገልፆ በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ ግን በግልፅ አልጠቀሰም፡፡
በሃገሪቱ ኢንተርኔት ተዘግቶ ተቃዋሚዎች ድምፃቸውን ለዓለም የሚያሰሙበትን መንገድ እንዳጡም ኤጀንሲው ይፋ አድርጓል፡፡
ትናንት የኢራን ፍትሕ ተቋም ቃል አቀባይ ጎላም ሁሴን ኢስማኤል ቀድሞ በኢራን የነበረው ውጥረት ቀነንሶ ተዘግተው የነበሩ ባንኮች ዋናዋና መንገዶችና ሱቆች ተከፍተዋል ቢሉም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ የሃገሪቱ ፖሊስ አሽከርካሪው ባለበት የመኪና መስታወት ሲሰብሩ ያሳያል፡፡  
አነጣጥሮ ተኳሾች ምለትም ስናይፐሮች ወደ ተቃዋሚዎች ጥይት መተኮሳቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ዋቢ በማድረግ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡




Post a Comment

0 Comments