ግብፅ በ2ቢልዮን ዶላር ወጪ ከ20 በላይ ሱ-35 የጦር ጀቶችን ለመሸመት ከሩስያ ጋር መፈራረሟ
ይታወሳል፡፡
የተያዘው የፈረንጆች አመት ከመጠናቀቁ
በፊት ግብፅ ካከናወነቻቸው ስምምነቶች መካከል ረብጣ ዶላሮችን በመመደብ የጦር መሳሪያዎችን መግዛት ነው፡፡
በቅርቡ እንኳን ሃገሪቱ በ2ቢልዮን
ዶላር ወጪ ከ20 በላይ ሱ-35 የጦር ጀቶችን ከሩስያ ለመሸመት መስማማቷ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎ ልዕለ ኃያሏ ሃገር
አሜሪካ በግብፅ ላይ ማእቀብ ልትጥልባት ትችላለች መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ማእቀቡ ግብፅ በስምምነቷ መሰረት
ግዢውን ከፈፀመች በቀጣይ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ግዢ እንዳትፈፅም የሚከለክል መሆኑን የአሜሪካ ባለስልጣንን ዋቢ በማድረግ
የአልጀዚራ ዘገባ አትቷል፡፡
በግብፅ እና በሩስያ መካከል የተደረገው
የጦር ጀት ግዢ እንዳይፈፀም አሜሪካ ከአራት ቀናት በፊት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለግብፅ ልካ እንደነበር የዘገበው ደግሞ ብሉምበርግ
ነው፡፡
የትራምፕ አስተዳደር ከግብጹ ፕሬዝዳንት
አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዲኖር ሲሰራ ቢቆይም በአንፃሩ ደግሞ ሩስያ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ላይ
ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት እያሰፋች በመምጣቷ በአሜሪካና በግብፅ መካከል የሚያኮራርፍ ሁነት እየተፈጠረ መሆኑን ብሉምበርግ በዘገባው ጠቅሷል፡፡
የአሜሪካ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ጉዳየች
ምክትል ቃል አቀባይ አር ክላርክ ኩፐር ‹‹ጉዳዩ አዲስ አይደለም፤ ማእቀቡ ግብፅን ከባድ ሁኔታ ውስጥ ይከታታል፤ይህን ደግሞ ካይሮ
ጠንቅቃ ታውቀዋለች አዲስ ዜና አይደለም›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
አሜሪካ ለግብፅ ምጣኔ ሃብት እድገትና
ወታደራዊ ጡንቻ መፈርጠም በቢልዮን ዶላሮች የሚገመት ድጋፍ በየዓመቱ እንደምታደርግ ይታወቃል፡፡ የሁለቱ ሃገራት መቃቃር ይህን የመተባበር
ስሜት ሊጎዳው እንደሚችል ይታመናል፡፡
የቀይ ባህር የመርከቦች መተላለፊያ
መስመር ሲዊዝ ካናልን በባለቤትነት የምታስተዳድረው ግብፅ አሜሪካ ባሰበችው ማእቀብ ዙሪያ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ
የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን