ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ ኮርፖሬት የፌስቡክ ገፅ waltainfo.com በ03/04/12 ዓ.ም "ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካዔል ጋር በተያያዘ ከተቋማችን እውቅና ውጪ ሀሰተኛ መረጃ መለቀቁ ይታወሳል፡፡"
ይህንን ተከትሎም ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ ኮርፖሬት ወዲያውኑ ለተፈጠረው ክስተት ይቅርታ መጠየቁ እና ጉዳዩን አጣርቶ እንደሚገልፅ አስታውቆ ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ዋልታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
በመሆኑም ሁኔታውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና ፖሊስ እየመረመሩት ይገኛል፡፡
የምርመራ ውጤቱን መጨረሻ እንደምንገልፅ የተጠበቀ ሆኖ ተቋማችን ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ብሎ በጠረጠራቸው አራት የተቋሙ ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል፡፡
ዛሬ የዋልታ የስራ አመራር ቦርድና ማኔጅመንት አባላት ክስተቱ ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ የተደረገውን ማጣራት መነሻ በማድረግ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ሰራተኞቹ ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ እንዲታገዱ ወስነዋል፡፡
"በቀጣይም ከአስተዳደራዊ እርምጃ ባለፈ የፍትህ አካላት ድርጊቱን በፈፀሙት አካላት ላይ አጣርቶ በሀገሪቱ ህግ መሰረት የሚወስዱትን እርምጃ ተከታትለን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ድርጅታችን በሀገሪቱ የሚዲያ ኢንዱስትሪ ውስጥ እየፈጠረ ያለውን በጎ ተፅዕኖ በእውነትኛ መረጃ እና የህዝብን ድምፅ ባከበረ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እናረጋግጣለን!!"
ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን