የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ በትግርኛ ምህፃሩ ዴምህት ራሱን አክስሞ ከህወሓት ጋር በመዋሃድ ለመታገል መወሰኑ አስታወቀ፡፡ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት በበኩሉ የዴምህትን ውሳኔ አድንቋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) ራሱን አክስሞ ከህወሓት ጋር በመዋሃድ ለመታገል መወሰኑ አስታወቀ፡፡ የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ መኮንን ተስፋይ ለዶቼቨለ DW እንዳሉት ድርጅታቸው ራሱን አክስሞ ከህወሓት ጋር ለመዋሃድ የወሰነው ወቅታዊ የኢትዮጵያ ፓለቲካዊ ሁኔታ በመገምገም ነው፡፡
የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት በበኩሉ የዴምህትን ውሳኔ አድንቋል፡፡
በኢትዮጵያ ከተደረገው የፖለቲካ ለውጥ በኋላ ከሀገራቸው ውጭ ሆነው በትጥቅ ትግል ጭምር መንግስትን ለመጣል ይንቀሳቀሱ ከነበሩ ሐይሎች መካከል ወደ ሀገር እንዲገቡ ጥሪ መተላለፉ ተከትሎ፣ ከኤርትራ ከተመለሱ ሽምቅ ተዋጊዎች መካከል ከፍተኛ ጦር ይዞ የተመለሰው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ ሰሞኑን እንደገለፀው ራሱን አክስሞ ከህወሓት ጋር ተዋህዶ ለመስራት መወሰኑ አስታውቋል፡፡
ባለፈው ዓመት ወርሐ መስከረም ወደ ኢትዮጵያ እስከ ተመለሰበት ድረስ ለ18 ዓመት ገደማ ማእከሉ ኤርትራ አድርጎ የትጥቅ ትግል ያደርግ የነበረው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) እንደሚለው ድርጅቱ ከህወሓት ጋር በጋራ ለመስራት የወሰነው በንቅናቄው ስራ አስፈፃሚና ማእከላይ ኮሚቴ ደረጃ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ መሆኑ የዴምህት ሊቀ መንበር አቶ መኮንን ተስፋይ ለዶቼቨለ ገልፀዋል፡፡
ሊቀመንበሩ አቶ መኮንን እንደሚገልፁት በትግራይ ህዝብ ላይ ያንዣበቡ አደጋዎች እየተበራከቱ ነው፡፡ በዚህም "የተፈጠረው ሁኔታ ለማለፍ ዴምህት ራሱን አክስሞ ከህወሓት ጋር ተዋህዶ ለመስራት ወስንዋል" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አቶ መኮንን ጨምረውም ዴምህት ከህወሓት ጋር ከዴሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ውጭ ሌላ ልዩነት አልነበረውም ብለዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ዙርያ ማብራርያ የሰጡት የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደሩ ቢሮ ሐላፊ አቶ ተኪኤ ምትኩ የዴምህት ውሳኔ አድንቀዋል፡፡
ሐላፊው እንደሚሉት የንቅናቄው ውሳኔ "በአስቸጋሪ ወቅት የትግራይ ህዝብ እየተባበረ እንደሚሄድ መልእክት ያስተላለፈ" ብለውታል፡፡
ከ2 ሺህ በላይ የሚገመቱ ታጋዮች የነበሩት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዴምህት አባላቱ በትግራይ ክልል ፖሊስ ጨምሮ በተለያዩ የግልና መንግስት ስራዎች ተሰማርተው መስራት መጀመራቸው ገልፅዋል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የንቅናቄው አባላት ድጋፍ እንዲደረግላቸው ከመንግስት ጋር መግባት ላይ መደረሱን ዴምህት አስታውቋል፡፡
DW አማርኛ እንደዘገበው
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን