በደብረ ብርሃን የኢንቨስትመንት ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ አስተዳዳሪ ገለፁ።
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶተፈራ ወንድማገኘሁ እንዳሉት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በከተማዋና በዞኑ መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ ለማድረግ የሚፈልጉ ባለሃብቶች መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል።
በተያዘው በጀት ዓመት 236 ባለሀብቶች ነዋያቸውን በዞኑ ፈሰስ እንዲያደርጉ ታቅዶ በአምስት ወራት ውስጥ 247 ባለሀብቶች ፍላጎት ማሳየታቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ገልፀዋል።
ይህም አፈፃፀሙ 104 ነጥብ 7 በመቶ ሆኗል ብለዋል አቶ ተፈራ።
ደብረ ብርሃንን "ሃገራዊ እሴትን የጠበቀች ለነዋሪዎቿ ምቹ ስልጡን ከተማ (Smart city) ለማድረግ ከነዋሪዎቿ ጋር ምክክር ሲደረግ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው ባለሀብቶች የዞኑን ሃብት ሲጠቀሙ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሚኪያስ ቴዎድሮስ በዞኑ የቱሪዝም ፍሰት እየጨመረ መምጣቱን እና የጎብኝዎች አማካኝ የቆይታ ጊዜ መጨመሩን ለዋልታ ገልፀዋል።
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን