*ይህ የተፃፈው በተለይ የጋዜጠኝነትን ሙያ ለሚያውቁ ነው።
*********************************************
በመጀመሪያ ድርጊቱ በጣም ያሳፍራል! ማንም ያድርገው ማን አስነዋሪ ነው!
ሲቀጥል መረጃ ሲወጣ እውነትነቱን ማጣራት ቢያንስ የተዛባ(ሀሰተኛ መረጃ) ከመያዝ ያድናል።
ሀሰተኛ መረጃዎችን እንከታተላለን የሚሉ ጋዜጠኞች ጭምር ሚዛናዊ ያልሆነ መረጃዎችን ሲያጋሩ እያየን ነው(ቀድሞ "በስልክ ደውዬ እንደነገሩኝ" ይለን የነበረ ጋዜጠኛ ሳይቀር "ለምን አላችሁ?" ብሎ ሳያጣራ መረጃዎችን ሲለጥፍ እያየን ነው።
ልብ በሉልኝ "ደውዬ እንደነገሩኝ" የሚለው ጋዜጠኛ "ሀሰተኛ መረጃ" ብሎ በሚለጥፈው መረጃ ላይ የኃላፊዎችን ፊርማ፣ የኢሜል አድራሻ፣ ደብዳቤ የተፃፈበት የፊደል አጠቃቀም ወዘተ. ን በተመለከተ ሲመረምር ይታወቃል። እዚህኛው መረጃስ ስለምን ያን ሳያደርግ ቀረ?
ሌሎቻችን(በተለይም ሙያውን አጥንተናል የምንል ሰዎች ) እንዴት የመረጃን እውነታ ማጣራት ተሳነን?
እስኪ በዋልታ የፌስቡክ ገፅ ስለተለጠፈው የሐሰት መረጃ ልብ ብለን እንየው
*በመጀመሪያው መስመር ላይ "የትግራይ ክልል #ር'ስ'ሰ_መስተዳድር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን...." ይላል። "አፍቃሬ ሕወሓት" ሲባል የነበረ ጣቢያ እንዴት የደብረጽዮን(ዶ/ር)ን ስልጣን ማወቅ ያቅተዋል? የፊደላት ስህተትስ?
*በሁለተኛውና ሶስተኛው መስመር ላይ "መቀለ ከሚገኘው ሪፖርተራችን ሰምተናል።" ይላል የዋልታ ፌስ ቡክ ገፅ ዜናዎችን ለሚከታተል ሰው ይህ የዋልታ የምንጭ አጠቃቀም እንዳልሆነ ጠንቅቆ ይረዳል ብዬ አስባለሁ።
በዚህ ስልት እንኳን ተፃፈ ቢባል የሪፖርተሩ ስም #የግድ ይጠቀሳል እንጂ ሪፖርተራችን ተብሎ ብቻ አይፃፍም(የቀድሞ ዘገባዎችን መለስ ብሎ ማረጋገጥ ይቻላል።)
*አምስተኛው መስመር ላይ"ዋልታ ኢንፎረሜሽን መአከል..." እያለ ይቀጥላል። ዋልታ ስያሜዉን ከቀየረ(ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ከተባለ) ሶስት ዓመት ገደማ ሆኖታል።
ይህንንም ደብዳቤ የሚልኩ ተቋማት እንኳን ጠንቅቀው ያውቁታል።
እና ውሎዉን ተቋሙ ላይ ያደረገ ሰራተኛ ለዚያውም የዜና ዘጋቢ የሚሰራበትን ተቋም ስም እንዴት ሊስት ይችላል?
'ፈጣን የመረጃ አጣሪ' ጋዜጠኞች እንዴት ይህን መጠርጠር አልቻሉም? እንዴትስ ማጣራት ተሳናቸው?
ጉዳዩ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚለውን በጋራ እንሰማ ይሆናል። ያ እስኪሆን ግን ቢያንስ ያልተጣሩ መረጃዎችን ከመፃፍ ብንቆጠብ(በተለይ ጋዜጠኞች)
ድርጊቱ ግን እጅግ አሳፋሪ ነው!

0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን