👉" 16 ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ግጭት ተከስቷል 35 ሺ ተማሪዎች ወደ ቤት ተመልሰዋል።" የጠ/ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ #ንጉሱ ጥላሁን ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም
********************
👉"የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረትም ስልካቸው ዝግ በመሆኑ አልተሳካም።"
#ቢቢሲ አማርኛ ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም
👉"ከአንድ ወር ከሁለት ሳምንት በፊት ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ጋምቤላ በመጓዝ ሳሉ ሱድ ተብላ በምትጠራው አካባቢ የታገቱት 17 ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም በቂ መረጃ ያልተገኘበት እና በአካባቢው ባለው የቴሌኮም አገልሎት መቋረጥ ለመከታተል አዳጋች ሆኖ ቀጥሏል፡፡"
#አዲስ_ማለዳ ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም
👉"በየጊዜው የምናገኘውን መረጃ ለህብረተሰቡ እናደርሳለን።"
አቶ ንጉሱ ጥላሁን ቅዳሜ ጥር 2/2012 ዓ.ም በኢቴቪ።
************** ****************
👉"ልጆቹ #በሰላም እንዲፈቱ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። በዚህም ታግተው ከነበሩ ተማሪዎች ውስጥ 21 ተማሪዎች (13 ሴቶችና 8 ወንዶች) ተለቀዋል።
6 ተማሪዎች (አንዱ የአካባቢው ተማሪ ነው) አሁንም ታግተዋል። ቀሪዎቹን ታጋቾች ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው።"
አቶ ንጉሱ ጥላሁን ቅዳሜ ጥር 2/2012 ዓ.ም በኢቴቪ።
👉“ከሸማቂዎቹ ጋር የሚደረግ ድርድር የለም”
#የኦሮምያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃልፊ አቶ ታዬ ደንደአ
#ቪኦኤ ጥር 01ቀን 2012 ዓ.ም
👉"የሸማቂዎቹ የምሥራቅና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ መሪ “በእርምጃው #እየተጎዳ ያለው ህዝቡ ነው” ብለዋል።"
#ቪኦኤ ጥር 01ቀን 2012 ዓ.ም
************** ******************
👉"በምዕራብ ኦሮሚያ አንድ ወር ከሁለት ሳምንት በፊት ስለታገቱት 17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ፡፡"
#አዲስ_ማለዳ ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም
👉"የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ፕሬስ ሴክሬታሪ ባልደረባ ሔርሜላ ሰለሞን በተባለው ቀን ምንም አይነት መግለጫ እንደማይሰጥ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።"
#አዲስ_ማለዳ ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን