ታህሳስ 03/2012 ዓ.ም ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በተቋሙ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ በተሰራጨው ሃሰተኛ ዜና ምክንያት ገጹን የሚያስተዳድሩ የነበሩ 7 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ጥር 01/2012 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተደራጁ ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር አበራ ቡሊና እንዳሉት ታህሳስ 3 ቀን ከሰዓት ብኋላ 11 ሰዓት አካባቢ በተቋሙ የፌስ ቡክ አካውንት ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እንዳረፉ ተደርጎ በተሰራጨው የሃሰት ዜና ገጹን የሚያስተዳደሩት 7 ሰራተኞች ዜናውን ማስቀረት ሲችሉ ይህን ባለማድረጋቸው ተጠያቂ ሆነዋል።
እንደኮማንደሩ ገለጻ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸውም እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
AS ዘ ብሔረ ጦቢያ
0 Comments
ሐሳቦን ያጋሩን