"የመረጃ ነፃነቱ እና ምላሽ ያጡ የህዝብ ጥያቄዎች"

.................. "አልተሳካም" ...................


በተለይም የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ከፈረሰ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ ለማግኘት የሚደረጉ ሙከራዎች እጅጉን ፈታኝ እየሆኑ መጥተዋል፡፡
በየ ዓመቱ የመረጃ ነፃነትን በዓል የምታከብረው ሃገሬ መረጃ የመስጠት አቅሟን አጥታለች፡፡
መረጃ አንሰጥም ባዮችም ያለ ጠያቂ እንዳሻቸው እያደረጉ ማየት ተለምዷል፡፡
እስኪ ያልተሳኩ (ምላሽ ያጡ) የህዝብ ጥያቄዎችን በጥቂቱ ልጋብዛችሁ፡፡
..................................................................................
‹‹ጉዳዩን ለማጣራት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሐመድ አምደኒል ጋር ብንደውልም ስልክ አያነሱም።››
ዶቼ ቬለ (DW)

"ሸገር ተማሪዎቹ ስላሉበት ሁኔታ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ለመጠየቅ ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካለትም፡፡"
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

‹‹የስልክና የኢንትርኔት አገልግሎቶች ለምን እንደተቋረጡ ለማወቅ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ ሪጅን ብንደውልም ምላሽ የሚሰጠን በማጣታችን ጥረታችን አልተሳካም።››
ቢቢሲ አማርኛ

"በዚህ ጉዳይ ላይ የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮን ለማናገር ያደረግነው ጥረትም አልተሳካልንም፡፡"
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

"ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ምን እንደሚል ለመስማት ስልክ ብንደውል፣ ስልካቸው አይሰራም፡፡"
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

"ሸገር በአካባቢው የኔትዎርክ ብልሽት ያለ እንደሆነ እንዲነገረው ኢትዮ ቴሌኮምን ቢጠይቅም መልስ አላገኘም፡፡"
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

"የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ከእገታ የተለቀቁትንና ያልተለቀቁትን ተማሪዎች ማንነት ከዩኒቨርስቲው ለማጣራት ጥረት ባደርግም ስልክ አልሰራ ስላለኝ ጥረቴ አልተሳካም ሲል ተናግሯል፡፡"
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ሰናይት ዳምጤን ጨምሮ ፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ስለ ጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ተገቢ ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም።››
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

‹‹አፈፃፀም ላይ ክፍተት ይሥተዋልበታል የተባለው ም/ቤቱ ለዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ምክትል አፈጉባኤዋን ብንጠይቅም ምላሽ ሳይሰጡን ቀርተዋል፡፡››
ዋልታ ቴቪ

‹‹በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በጉዳዩ ዙሪያ መልስ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም።››
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

‹‹ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰራው የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም።››
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

‹‹በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት የጠየቅናቸው የክልሉ ፕሬስ ሰክሪታሪ ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡››
አሐዱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን

‹‹የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገስጥ አሳምናቸውን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ደረስ አልተሳካም።››
አስራት ሚዲያ ሀውስ

‹‹በጉዳዩ ዙሪያ የደቡብ ክልል መንግስት አስተያየትን ለማካተት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡››
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

‹‹ጠፍቷል ስለተባለው የሰው ህይወት፣ ንብረትና አሁን ላይ ስላለው የፀጥታ ሁኔታ ለመጠየቅ አሐዱ ወደ ክልሉ ባለሥልጣናት ያደረገው የስልክ ጥሪ አልተሳካም፡፡››
አሐዱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን

‹‹የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ትራንስፖርት ቢሮን ጨምሮ የተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማትን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።››
ዶቼ ቬለ (DW)

‹‹ቢቢሲ ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ ከጥቂት ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በተመለከተ ከአንድ የቤተሰብ አባላቸው ለማረጋገጥ ቢችልም ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንና የጸጥታ ኃላፊዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።››
ቢቢሲ አማርኛ

‹‹የተማሪዎች መለቀቅ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ማብራሪያ የሰጡት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተለቀቁ ያሏቸው ተማሪዎች አሁንም ባሉበትን ሁኔታ እንደሚገኙ ለመጠየቅ ያደረግነው ሙከራም አልተሳካም።››
አስራት ሚዲያ ሀውስ

‹‹ጉዳዩን በተመለከተ DW የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።››
ዶቼ ቬለ (DW)

ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ ለማጣራት ያደረግኩት ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካልኝም፡፡ እስኪሳካ ድረስ መጠየቄን እንደማልተው፤ ሲሳካም ጀባ እንደምላችሁ አይ ፕሮሚስ!

Post a Comment

0 Comments