ጀዋር መሐመድን ጨምሮ 18 ተጠርጣሪዎች ወደ ወሕኒ ቤት ሊወርዱ ነዉ፡፡


ጀዋር መሐመድ
አቶ ጀዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ 18 ተጠርጣሪዎች ከፖሊስ ማረፊያ ወጥተው ወደ መደበኛ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ፍርድ ቤት አዘዘ፡፡ ተከሳሾች ዛሬ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት ለዛሬ እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዞ የነበረው አቶ ደጀኔ ጣፋ እና መስተዋርድ ተማም ዛሬም ባለመቅረባቸው ክሱ ሳይነበብ ቀርቷል፡፡ ከዚህ ቀደም በሌላ መዝገብ ተከሰዉ የነበሩት ሁለቱ ተከሳሾች የቀድሞዉ መዝገባቸው ተዘግቶ ክሱ፣ በነጀዋር መሐመድ መዝገብ እንዲጠቃለል ፍርድ ቤቱ ማዘዙን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለዶይቼ ቨሌ ተናግረዋል፡፡

ተከሳሾቹ ወደ መደበኛ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ፍርድ ቤት ማዘዙን በመቃወም ጠበቆቻቸው በተለይ ለአቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሃምዛ አዳነ ጥብቅ ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ ቢጠይቁም፤ አቃቤ ህግ በዜጎች መካከል ልዩነት መፈጠር የለበትም በሚል የተለየ ጥበቃ አያሻቸም ሲል ተከራክሯል፡፡ 

ተከሳሾችም የትም ቢታሰሩ ግድ እንደሌላቸዉ ከገለጹ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ሁሉም ተከሳሾች ወደ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ አዝዟል። ፍርድ ቤቱ በዛሬ ችሎቱ  እስካሁን ያልቀረቡ ተከሳሾች / ፀጋዬ ረጋሳ፣ አቶ ደጀኔ ጉተማ እና ዶር ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ይዞ እንዲያቀርባቸው፤ ከሌሉም ፖሊስ ማብራሪያ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ካዘዘ በኋላ ለመስከረም 21 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጥሮ ሰጥቷል።

DW (ዶቼ ቬ ሌ)


AS ዘ ብሔረ ጦቢያ

Post a Comment

0 Comments